avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
27.02.2026 20:27
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለሽብር ተከሳሹ ዶ/ር ሲሳይ አውግቼው የፈቀደውን የ100 ሺህ ብር ዋስትና፤ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጊዜያዊነት አገደ።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዋስትናውን ያገደው፤ የፌደራል ዐቃቤ ህግ ለይግባኝ ሰሚ ችሎት ባቀረበው አቤቱታ ላይ ብይን እስኪሰጥ ድረስ ነው።

የአማራ ክልልን ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት “በመግደል”፤ የክልሉን ቀጥሎም የፌዴራሉን መንግሥት ስልጣን “በኃይል ለመቆጣጠር” በማሰብ “የሽብር ድርጊት ፈጽመዋል” በሚል ክስ ከቀረበባቸው 51 ተከሳሾች ውስጥ አንዱ የሆኑት ዶ/ር ሲሳይ፤ ዋስትና የተፈቀደላቸው ባለፈው ሰኞ ዕለት ነበር።

ተከሳሹ የዋስትናውን ሂደት አጠናቅቀው ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የተለቀቁት ከትላንት በስቲያ ረቡዕ ከሰዓት 10 ሰዓት ገደማ ነው።

ሆኖም በዚሁ ዕለት ዶ/ር ሲሳይ ሊቀበሏቸው ሲጠብቋቸው ከነበሩ ቤተሰቦቻቸው ጋር ሳይገናኙ፤ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት “በር ላይ ሆነው በጠበቋቸው” ፖሊሶች ተይዘው መወሰዳቸውን ጠበቃቸው አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረው ነበር።

ተከሳሹ “ወደ ፌደራል ፖሊስ እየተወሰዱ” መሆኑን ለቤተሰቦቻቸው እንደተናገሩም በወቅቱ ተገልጿል።

ዶ/ር ሲሳይ በእርግጥም በዕለቱ የተወሰዱት፤ በአዲስ አበባ ሜክሲኮ አደባባይ አቅራቢያ ወደሚገኘው የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ የእስረኞች ማቆያ መሆኑን ጠበቃ ሰለሞን አረጋግጠዋል።

ደንበኛቸው በትላንትናው ዕለት በጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በአካል ቀርበው እንደነበርም አመልክተዋል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17590/

@EthiopiaInsiderNews
10
😁 7
😢 3
👍 1
3 9K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram