avatar
Ethiopia Insider
Переслано от канала
26.02.2026 17:01
የዲጂታል የመራጮች ምዝገባ ተስፋና ስጋት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለመጪው 7ተኛ ሀገራዊ ምርጫ የዲጂታል መራጮች ምዝገባ ስርዓት ሊተገበር መሆኑን ማስታወቁን ተከትሎ፣ ይህ አዲስ አሰራር ከሚሰጠው ተስፋ ጎን ለጎን ስጋትንም ፈጥሯል። ቦርዱ ቴክኖሎጂው ሂደቱን ለማቀላጠፍ፣ ጊዜና ጉልበት ለመቆጠብ እንዲሁም አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ እንደሚረዳ ይፋ ቢያደርግም፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ግን በቅርቡ ባጠናቀቁት የዕጩዎች ዲጂታል ምዝገባ ላይ ያጋጠሟቸውን ችግሮች በመጥቀስ ስጋት እንዳላቸው ይገልጻሉ።


ፓርቲዎቹ እንደሚሉት፣ የዕጩዎች ምዝገባ ላይ የነበረው የሲስተም እና የኢንተርኔት ተደራሽነት ችግር እንዲሁም የማጽደቅ ሂደቱ መዘግየት ከፍተኛ የጊዜና የሀብት ብክነት አስከትሏል። በመሆኑም በሚሊዮን የሚቆጠሩ መራጮችን በዲጂታል ለመመዝገብ መታቀዱ ተመሳሳይ እንቅፋቶች እንዳይፈጠሩ ሰፊ ዝግጅትና የሙከራ ስራዎች መከናወን እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል። በዓለም አቀፍ ተሞክሮ መሰረትም የዲጂታል ምዝገባ ማጭበርበርን ለመከላከል ቢረዳም፣ ከሳይበር እና የግል መረጃ ደህንነት ጋር የተያያዙ ስጋቶችን በአግባቡ ታሳቢ ማድረግ እንደሚገባ ጥናቶች ያሳስባሉ።

🔴ሙሉ ትንታኔውን ለማንበብ ➡️ https://ethioelections.com/የዲጂታል-የመራጮች-ምዝገባ-ተስፋና-ስጋት/
#ምርጫ2018 #EthiopiaElection #digitalregistration
10
👍 3
3 7.6K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram