avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
26.02.2026 13:21
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ አምስት የምርጫ ክልሎች ከትግራይ ክልል ውጭ ሆነው በቀጥታ የፓርላማ ምርጫ እንዲካሄድባቸው በተላለፈው ውሳኔ ላይ ጊዜያዊ የእግድ ውሳኔ አስተላለፈ። ፍርድ ቤቱ እግዱን ያስተላለፈው ከዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ፓርቲ የቀረበውን የእግድ አቤቱታ ተከትሎ ነው።

ስምረት ፓርቲ አቤቱታውን ለፍርድ ቤቱ ያቀረበው በፕሬዝዳንቱ አቶ ጌታቸው ረዳ በኩል ነው። ዛሬ ሐሙስ የካቲት 19፤ 2018 ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ለቀረበው አቤቱታ ተከሳሽ ወይም ተጠሪ የተደረገው ደግሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መሆኑን አቶ ጌታቸው በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ያጋሩት የፍርድ ቤት ሰነድ አመልክቷል።

ምርጫ ቦርድ በፍርድ ቤት አቤቱታ የቀረበበት፤ በትግራይ እና በአማራ ክልሎች መካከል “አከራካሪ ሆነው” የቆዩ የተባሉ አምስት የምርጫ ክልሎችን በተመለከተ ባለፈው ሰኞ ይፋ ባደረገው ውሳኔ ነው። እነዚህ የምርጫ ክልሎች ሁመራ፣ አዲ ረመጽ፣ ጠለምት፣ ኮረም ኦፍላ እና ራያ አላማጣ ናቸው። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

🔴ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17575/

[በዚህ ዘገባ ላይ ከቆይታ በኋላ ተጨማሪ መረጃ ታክሎበታል]

@EthiopiaInsiderNews
👎 7
4
👍 1
🥰 1
😁 1
10 7.5K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram