ከትላንት በስቲያ ሰኞ 100 ሺህ ብር ዋስትና በማስያዝ ከእስር እንዲፈቱ በፍርድ ቤት የተበየነላቸው ዶ/ር ሲሳይ አውግቼው፤ በዛሬው ዕለት ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በመውጣት ላይ እንዳሉ “በር ላይ ሲጠብቋቸው በነበሩ ፖሊሶች ተይዘው መወሰዳቸውን” ጠበቃቸው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ።
ተከሳሹ “ወደ ፌደራል ፖሊስ” እየተወሰዱ መሆኑን፤ ሊቀበሏቸው ሲጠብቋቸው ለነበሩ ቤተሰቦቻቸው አሳውቀዋል ተብሏል።
ዶ/ር ሲሳይ በአማራ ክልል ከሚንቀሳቀሰው የፋኖ ታጣቂ ቡድን ጋራ በመሆን “የአማራ ክልልን ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በመግደል የክልሉን ቀጥሎም የፌዴራሉን መንግሥት ስልጣን በኃይል ለመቆጣጠር በማሰብ የሽብር ድርጊት ፈጽመዋል” በሚል ክስ ከቀረበባቸው 51 ተከሳሾች ውስጥ አንዱ ናቸው።
በዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ ስር የሚገኙት እነዚህ ተከሳሾች
“የሽብር ክስ” የቀረበባቸው በሰኔ 2015 ዓ.ም ነበር።
አምስት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በተካተቱበት በዚህ ክስ ስር ካሉ ተከሳሾች ውስጥ በቅርቡ “የሰላም አማራጭ መቀበላቸውን” ያሳወቁትን ኮሎኔል ፋንታሁን ሙሃባውን ጨምሮ የሃያ ስምንቱ ጉዳይ ሲታይ የቆየው በሌሉበት ነበር።
የተከሳሾቹን ጉዳይ ሲመለከት የቆየው፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ህገ መንግስታዊ እና የሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
ዶ/ር ሲሳይ የ100 ሺህ ብር ዋስትና በማስያዝ ከእስር እንዲለቀቁ፤ ከትላንት በስቲያ ሰኞ የካቲት 16፤ 2018 በዋለው ችሎት ብይን መሰጠቱን ጠበቃው አስረድተዋል።
ለዋስትና የተጠየቀውን ገንዘብ የተከሳሽ ቤተሰቦች በዚያኑ ቀን ረፋድ ላይ መክፈላቸውን የገለጹት አቶ ሰለሞን ገልጸዋል።
🔴ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17568/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram