avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
25.02.2026 13:57
በትላንትናው ዕለት የምዝገባ ምስክር ወረቀቱ የተሰረዘው “አዲስ ስታንዳርድ” የበይነ መረብ መገናኛ ብዙሃን፤ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን “ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያዎች ተሰጥቶታል” የሚለው ክስ “ከእውነት የራቀ ነው” ሲል አስተባበለ።

የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (ሲፒጄ)፤ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የ“አዲስ ስታንዳርድ”ን ምዝገባ “በአፋጣኝ ወደነበረበት እንዲመልስ” እና በፕሬስ ላይ እያበረታ የመጣውን ጥቃት “እንዲያቆም” ጠይቋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የ“አዲስ ስታንዳርድ”ን የምዝገባ ምስክር ወረቀት መሰረዙን የገለጸው ትላንት ማክሰኞ የካቲት 17፤ 2018 አመሻሽ ላይ ባወጣው መግለጫ ነው።

ተቋሙ በትላንቱ መግለጫው፤ አዲስ ስታንዳርድ “የሚዲያ ስነ-ምግባርን፣ የኢትዮጵያን ህጎች እና የሀገርንና የህዝብን ብሔራዊ ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥሉ ዘገባዎችን በተደጋጋሚ በማሰራጨት ላይ ይገኛል” ሲል ከስሷል።

“[አዲስ ስታንዳርድ] በሚዲያ ዘርፉ ላይ የሙያ ስነምግባር እና የሀገርና የህዝብ ብሔራዊ ጥቅም አክብሮ እንዲሰራ ተደጋጋሚ ማሳሰቢያ እና ማስጠንቀቂያ ቢሰጠውም ለመታረም ፈቃደኛ አልሆነም” ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ወንጅሏል።

የአዲስ ስታንዳርድ ዋና አዘጋጅ አቶ ዮናስ ከድር፤ የተቆጣጣሪ መስሪያ ቤቱን ውንጀላ “ውድቅ ማድረጉን” መገናኛ ብዙሃኑ ዘግቧል። “አዲስ ስታንዳርድ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያዎች ደርሰውታል የሚለው ክስ ከእውነት የራቀ ነው። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙህን ባለስልጣን ቀደም ሲል ስለነበሩ የሕግ ጥሰቶችም ሆነ ስለተወሰዱ እርምጃዎች ለአዲስ ስታንዳርድ የዜና ክፍል በይፋ ያሳወቀው ነገር የለም” ሲል ዋና አዘጋጁ መናገሩን ዘገባው ጠቅሷል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️https://ethiopiainsider.com/2026/17565/

@EthiopiaInsiderNews
8
😢 2
😁 1
2 6.9K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram