በኦሮሚያ፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎች ያለው “የግጭት አውድ”፤ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ስራዎችን “ፈታኝ ማድረጉን” የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ።
ይሁንና ሰዎች አግቶ ከመሰወር ጋር በተገናኘ ያለው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ “እየቀነሰ” መሄዱን የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ ገልጸዋል።
አቶ ብርሃኑ ይህን ያሉት፤ ኢትዮጵያ የምታስተናግደው 16ኛውን የአፍሪካ ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ተቋማት ትስስር ጠቅላላ ጉባኤን አስመልክቶ ዛሬ ማክሰኞ የካቲት 17፤ 2018 በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።
ዋና ኮሚሽነሩ በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫቸው፤ በኢትዮጵያ ሰዎችን አስገድዶ መሰወር እና ገንዘብ መጠይቅ “የተለመደ” መሆኑን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ግን “ሰውን የሆነ ቦታ [አግቶ] አስቀምጦ ይሄን ያህል ብር አምጣ” ማለት መቀነሱን ገልጸዋል።
ይህ ተግባር የቀነሰው፤ ኢሰመኮ “በግጭት ዐውድ ውስጥ እና ከግጭት ዐውድ ውጪ” ባሉ አካባቢዎች ያደረገውን የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ ግኝቱን ይፋ ካደረገ ካለፈው ጥቅምት ወር ወዲህ እንደሆነ አቶ ብርሃኑ አስረድተዋል።
ብሔራዊው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋም ከአራት ወራት በፊት ጥቅምት ይፋ ባደረገው በዚሁ ግኝት፤ በአራት ክልሎች ባሉ መንገዶች ላይ በሚደርሱ ጥቃቶች፣ እገታዎች፣ የንብረት ዘረፋዎች እና ውድመቶች ምክንያት “የሰዎች ከቦታ ቦታ የመዘዋወር ነጻነት መብት አደጋ ላይ መውደቁን” ገልጾ ነበር።
በዚህ የኢሰመኮ ሪፖርት የተጠቀሱት ክልሎች አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች ናቸው።
🔴ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17559/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram