avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
23.02.2026 19:39
አቶ ጌታቸው ረዳ በፕሬዝዳትነት የሚመሩት ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ፓርቲ፤ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በምርጫ ክልሎች ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ “የሀገሪቱን ሕገ- መንግሥታዊ ሥርዓት መሠረት የሚንድ” ሲል ተቃውሟል። ውሳኔው “ተቋማዊ ነጻትን የሚደፈጥጥ” እና “ሕገ- መንግሥታዊ ሥርዓት አልበኝነትን የሚያውጅ ነው” ያለው ፓርቲው፤ የማስተካከያ እርምጃ ካልተወሰደ “በምርጫ የማይሳተፍ መሆኑን” አስታውቋል።

ፓርቲው ይህን ያለው፤ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ሰኞ የካቲት 16፤ 2018 በጻፈው ደብዳቤ ነው። የአቶ ጌታቸው ፊርማ ያረፈበት ደብዳቤው፤ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ እና እርሱን የተከተለው የምርጫ ቦርድ ድርጊት “ግልጽ የስልጣን አላግባብ መጠቀም” (abuse of Power) ማረጋገጫ እንደሆነ አመልክቷል።

በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 62 ስር ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የተሰጠው ስልጣን እና ተግባር “ከህገ-መንግስት ትርጉም እና የክልሎች ወሰን ክርክርን ከመፍታት አይዘሉም” ብሏል ፓርቲው። ምክር ቤቱ “የምርጫ ክልሎችን የማዋቀርም” ሆነ ክልሎችን “ከነባር አስተዳደራዊ መዋቅራቸው ውጭ” በፌዴራል መንግስት ስር እንዲሆኑ የመወሰን “ምንም አይነት ህገ-መንግስታዊ ውክልና” እንደሌለው ስምረት በደብዳቤው አስገንዝቧል።

ማንኛውም የክልል ወሰን መፍትሄ ሊያገኝ የሚገባው በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 48 መሰረት መሆኑን ያመለከተው ፓርቲው፤ ይህ ሂደት ሳይጠናቀቅ እና በህዝበ-ውሳኔ ይፋዊ ለውጥ ሳይደረግ “ምርጫው በፌዴራል መንግስት ይፈጸም” መባሉ “የክልል አስተዳደርን በጉልበት የመንጠቅ ሙከራ ነው” ሲል አውግዟል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17542/

@EthiopiaInsiderNews
11
👏 3
🤔 2
💩 1
9 7.3K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram