የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፤ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ የክልሉን ህገ መንግስታዊ ወሰን “አደጋ ላይ የሚጥል ነው” ሲል አወገዘ
በትግራይ ክልል ስር የነበሩ አምስት የምርጫ ክልሎች “በቀጥታ” ምርጫ እንዲካሄድባቸው የተላለፈውን ውሳኔ፤ “በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያገኘውን የትግራይ ህገ መንግስታዊ ወሰን አደጋ ላይ የሚጥል ነው” ሲል የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አወገዘ። ውሳኔውን “አደገኛ” ሲል የጠራው አስተዳደሩ፤ የሚያስከትለውን “መዘዝ” ከግምት ውስጥ በማስገባት “በድጋሚ እንዲጤን” እና “እንዲታረም” በጥብቅ አሳስቧል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ማሳሰቢያውን የሰጠው፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኞ የካቲት 16፤ 2018 ዕለት ላወጣው መግለጫ በሰጠው ምላሽ ነው። ምርጫ ቦርድ በዛሬው መግለጫው፤ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሁመራ፣ አዲ ረመጽ፣ ጠለምት፣ ኮረም ኦፍላ እና ራያ አላማጣ ምርጫ ክልሎች የሚደረገው ምርጫ “ከትግራይ ክልላዊ መንግስት ውጭ” እንዲደረግ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቆ ነበር።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፤ የትግራይ ህዝብ ድምጽ ባልተወከለበት የፌዴሬሽን ምክር ቤት የተላለፈው ውሳኔ “ህገ መንግስቱን እና የፕሪቶሪያን ስምምነት በግልጽ የሚጥስ ነው” ሲል ነቅፏል። የቀድሞው የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፤ የፌዴሬሽን ምክር ቤትም ሆነ የምርጫ ቦርድ ውሳኔ “የሃገራችንን ሰላም የበለጠ ከማወክ ውጭ ሌላ ትርጉም አላቸው ብዬ አላምንም” ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ተችተዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
🔴ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17542/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram