avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
23.02.2026 16:01
በትግራይ እና በአማራ ክልሎች መካከል “አከራካሪ ሆነው” የቆዩ የተባሉ አምስት የምርጫ ክልሎች፤ “የይገባኛል ጥያቄው እስከሚፈታ” ድረስ ከትግራይ ክልል ውጪ ሆነው ለፓርላማ “በቀጥታ” ምርጫ እንዲደረግባቸው ውሳኔ ተላለፈ። ውሳኔ የተላለፈባቸው የምርጫ ክልሎች፤ ሁመራ፣ አዲ ረመጽ፣ ጠለምት፣ ኮረም ኦፍላ እና ራያ አላማጣ ናቸው።

እነዚህ ምርጫ ክልሎች ከሁለቱ ክልሎች ውጭ ሆነው ምርጫ እንዲካሄድባቸው ውሳኔ ያሳለፈው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ነው። ለምክር ቤቱ ውሳኔ መንስኤ የሆነው፤ ጥር 22፤ 2018 ይፋ የተደረገው የምርጫ ክልሎች እና ምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በዚህ ዝርዝር ላይ በሁመራ ምርጫ ክልል የሚገኙ ጣቢያዎች፤ በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን፣ በሰቲት ሁመራ፣ ቃፍታ ሁመራ እና ወልቃይት ወረዳዎች የሚገኙ እንደሆነ ተጠቅሶ ነበር። በአዲ ረመጽ የምርጫ ክልል የሚገኙ ጣቢያዎችም በተመሳሳይ ሁኔታ በትግራይ ክልል፣ ምዕራባዊ ዞን፣ በወልቃይት እና ፀገዴ ወረዳዎች ውስጥ ያሉ መሆናቸው በዝርዝሩ ላይ ሰፍሯል።

በዚሁ ክልል፣ በተመሳሳይ ዞን ውስጥ እንደሚገኝ በምርጫ ቦርድ ዝርዝር ተጠቅሶ የነበረው የፀለምቲ ምርጫ ክልል፣ በፀለምቲ ወረዳ የሚገኝ መሆኑ በሰነዱ ተመልክቷል። በትግራይ ክልል፣ ደቡብ ዞን ስር ያሉ የምርጫ ክልሎች ሆነው የተጠቀሱት ደግሞ ኦፍላ ኮረም እና አላማጣ ናቸው። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17522/

@EthiopiaInsiderNews
👍 9
4
👎 3
😁 3
10 6.1K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram