ኢትዮጵያ “ከሶማሌ ጫፍ እስከ ምጽዋ ጫፍ” በባህር ላይ የሚያጋጥሙ ሽብሮችን የሚያስቀር፣ ቴክኖሎጂ የታጠቀ እና “ውጊያ የሚያሳጥር” ልዩ ኃይል (ኤሊት ፎርስ) እና ተቋም መገንባቷን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጠቀሱትን የመከላከያ ሰራዊት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ የሚመሩት ሌተናል ጄነራል ሹማ አብደታ በበኩላቸው፤ የጦር ክፍሉ መንግስት ለሚሰጠው “ማንኛውም ግዳጅ” ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢፌዲሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ የሆኑት አብይ ይህን ያሉት በሀዋሳ ስቴድየም ዛሬ እሁድ የካቲት 15፤ 2018 በተካሄደው፤ የመከላከያ ሰራዊት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ 65ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ማጠቃለያ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።
የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ፤ መደበኛው ጦር “ሊወጣቸው የማይችላቸውን” “ውስብስብ እና አስቸጋሪ” ግዳጆችን የሚፈጽሙ፣ የኮማንዶ፣ የአየር ወለድ እና የጸረ ሽብር ልዩ ኃይል አባላትን በውስጡ የያዘ ነው።
በሺህዎች የሚቆጠሩ የዕዙ አባላት፤ የበዓሉ የክብር እንግዳ እና የኢፌዲሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ፊት የሰልፍ እና ወታደራዊ ትርኢት አሳይተዋል።
የጸረ ሽብር ልዩ ኃይል አባላትም፤ ከሄሌኮፕተር በአየር ላይ በተዘረጋ ገመድ ላይ ተንጠላጥለው “ታጋቾችን ለማስለቀቅ” እንዴት “ግዳጅ እንደሚወጡ” የሚያሳይ ትርኢት ለታዳሚያን አቅርበዋል።
ሌተናል ጄነራል ሹማ በዛሬው ክብረ በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የዕዙ የምስረታ በዓል እንዲከበር ከተደረገባቸው ምክንያቶች አንዱ “ጠላቶቻችን አርፈው የማይቀመጡ ከሆነ ውጊያ ጨራሽ መሆናችንን ለማሳየት ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።
🔴ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17491/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram