avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
20.02.2026 21:01
ነዋሪነቱ በመቐለ ከተማ የሆነው ጋዜጠኛ፤ በትግራይ ክልል “ዳግም ጦርነት ሊቀሰቀስ ነው” የሚለውን ስጋት ተከትሎ “ሰዎች በብዛት እየወጡ” መሆኑን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጧል።

ከክልሉ ወደ አዲስ አበባ የሚደረጉ የአየርም፣ የየብስም ትራንስፖርት አማራጮች “በጣም ቢዚ ናቸው” ያለው ጋዜጠኛው፤ “በአውሮፕላንም፣ በባስም ብዙ ሰው እየወጣ ነው” ሲል ያለውን ሁኔታ ያስረዳል።

ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ቃላቸውን እንደሰጡት የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ሁሉ፤ ጦርነትን በመስጋት ከትግራይ ክልን በብዛት እየወጡ ያሉት ወጣቶች ስለመሆናቸው ይናገራል።

በፍጥነት መውጣት የሚፈልጉ ወጣቶች፤ በክልሉ የአውሮፕላን ትኬት ለማግኘት ቀናትን ላለመጠበቅ ሲሉ “ወደ አፋር ክልል ሰመራ በመኪና ሄደው ከዚያ በአውሮፕላን ይጓዛሉ” ይላል ጋዜጠኛው።

አውቶብስም እንደልብ እንደማይገኝ እና ትኬት ቆርጦ ለመሄድ ቀናትን ሊያስጠብቅ እንደሚችል የሚናገረው ጋዜጠኛው፤ በዚህ ምክንያት በመለስተኛ ተሽከርካሪዎች አቆራርጠው ወደ አፋር የሚገቡ ወጣቶች እንዳሉ ይገልጻል።

ወጣቶቹ “ትምህርትም ጭምር አቋርጠው ነው እየወጡ ያሉት” ሲልም የሁለተኛ ደረጃ እና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጭምር ከክልሉ እየሸሹ መሆኑን ያብራራል።

ዩኒቨርሲቲ የሚማር ወንድም እንዳለው የሚገልጸው ጋዜጠኛው፤ ቤተሰባቸው ትምህርቱን አቋርጦ ወደ አዲስ አበባ እንዲሄድ እየወተወቱት እንደሆነ በግል የገጠመውን አካፍሏል። “ትንሽ ሁኔታውን እንየው እና ካልሆነ ይሄዳል ብዬ ነው ያረጋጋኋቸው” ሲልም ቤተሰቡ በጭንቀት ላይ እንደሆነ ያክላል።

🔴ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17482/

@EthiopiaInsiderNews
😢 16
7
🕊 3
😁 1
🙉 1
13 7.2K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram