የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የግማሽ ቢሊዮን ዶላር ልዩ የውጭ ምንዛሬ ሽያጭ ጨረታ በነገው እለት ሊያካሄድ መሆኑን አስታወቀ። ባንኩ ተመሳሳይ መጠን ያለው የውጭ ምንዛሬ ለልዩ ጨረታ ሲያቀርብ፤ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሁለተኛው ነው።
ባንኩ ዛሬ አርብ የካቲት 13፤ 2018 ባወጣው መግለጫ፤ ፍላጎት ያላቸው ባንኮች ነገ ከረፋዱ አራት ሰዓት እስከ ቀኑ ስድስት ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ የጨረታ ሰነድ በማስገባት መሳተፍ እንደሚችሉ አስታውቋል። የጨረታው ውጤት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ይፋ እንደሚደረግም ባንኩ ገልጿል።
ብሔራዊ ባንክ ባለፈው ጥር 19፤ 2018 በተመሳሳይ ሁኔታ አውጥቶት በነበረው የግማሽ ቢሊዮን ዶላር ልዩ የውጭ ምንዛሬ ሽያጭ ጨረታ የንግድ ባንኮች ከፍተኛ ፍላጎት አሳይተው ነበር። በዚህ ጨረታ 31 ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን፤ የዶላር ፍላጎቱም ከአቅርቦቱ በ92.3 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ ነበረው።
በወቅቱ ለአንድ ዶላር የቀረበው ከፍተኛ ተመን 154.99 ብር ሲሆን፤ ዝቅተኛው ደግሞ 153.5 ብር መሆኑን ባንኩ ባወጣው መግለጫ አስታውቆ ነበር። ብሔራዊ ባንክ ከሶስት ቀናት በፊት ባካሄደው 18ኛ ዙር መደበኛ ጨረታ፤ ለአንድ ዶላር በቀረቡት ከፍተኛ እና ዝቅተኛ ተመኖች መካከል ያለው ልዩነት እጅግ የጠበበ ሆኗል።
🔴ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17480/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram