Dashen Bank @DashenBankEthiopia 08.04.2026 08:48 Скопировать Пожаловаться ቡና ባንክ ለዳሸን ባንክ 30ኛ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ ቡና ባንክ ዳሸን ባንክ የተመሰረተበትን 30ኛ አመት ምክንያት በማድረግ በዳሸን ባንክ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡ የቡና ባንክ ተወካዮች ባስተላለፉት መልዕክት ዳሸን ባንክ ባለፉት 30 ዓመታት በባንክ ኢንዱስትሪው መልካም ስም እንደፈጠረ አመልክተው ለወደፊት ከባንኩ ጋር ይበልጥ አብሮ ለመስራት የሚያስችሉ አማራጮች እንዳሉ አመልክተዋል፡፡ ተወካዮቹ ለዳሸን ባንክ ደንበኞች፣ ሠራተኞች እና ባለአክሲዮኖች እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡ የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተወካይና የባንኩ ቺፍ ስትራቴጂ ኦፊሰር አቶ አየለ ተሾመ በበኩላቸው መጪው ጊዜ በአገር በቀል ባንኮች መካከል ይበልጥ በትብብር መስራት እንደሚጠበቅ አመልክተው ዳሸን ባንክ ከቡና ባንክ ጋር አብሮ የሚሰራባቸው ዕድሎች ሰፊ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ ቡና ባንክ የዳሸን ባንክን 30ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ መልዕክት በማስተላለፉም ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ዳሸን ባንክ የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመት በተለያዩ መርሃ-ግብሮች እያከበረ ይገኛል፡፡ ❤ 20 👍 1 😁 1 1 3 6.2K
Обсуждение 1
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram