18.03.2026 13:21
ዳሸን ባንክ ከባቡል ኸይር በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር በድርጅቱ የኢፍጧር መርሃ-ግብር አዘጋጀ

የዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት "ሸሪክ" በባቡል ኸይር በጎ አድራጎት ድርጅት የኢፍጣር መርሃ-ግብር አዘጋጅቷል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የባንኩ የስራ ኃላፊዎች ዳሸን ባንክ ሸሪክ በታላቁ የረመዳን ወር ተቋሙ ድረስ የመጣው  አጋርነቱን ለማሳየት እንደሆነ ገልጸው ፤ ባንኩ በቀጣይም  ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ይሰራል ብለዋል።

የባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት መስራችና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሐናን አህመድ በበኩላቸው  ድርጅቱ በረመዳን ወር ብቻ 7 ሺህ የሚደርሱ አቅመ ደካሞችን እያስፈጠረ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ባቡል ኸይር በርካታ አቅመ ደካማ እናቶችን፣ ህጻናትና ሴቶችን ከምገባ ጀምሮ ፣ የሙያ ክህሎት እንዲኖራቸው እና ራሳቸውን እንዲችሉ እየሰራ ነው ብለዋል። በተጨማሪም አቅመ ደካሞች የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ እየሰራ እንደሆነም ገልጸዋል።

በበጎ አድርጎት ድርጅቱ በቋሚነት የሚደገፉ የአቅመ ደካሞች ቁጥር  ከ5ሺ በላይ እንደሆኑም ተናግረዋል።
20
👍 1
2 7.8K

Обсуждение 2

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Dashen Bank

88.6K
Dashen Bank is one of the leading banks in Ethiopia with over 900+ branches and banking outlets.
Visit our official facebook* site @ https://www.facebook*.com/DashenBankOfficial
Visit our Website:https://dashenbanksc.com
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram