Dashen Bank @DashenBankEthiopia 17.03.2026 21:26 Скопировать Пожаловаться ሳንቴ ሜዲካል ሴንተር ለዳሸን ባንክ 30ኛ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ ሳንቴ ሜዲካል ሴንተር ዳሸን ባንክ የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በዳሸን ባንክ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡ ሳንቴ ሜዲካል ሴንተርን በመወከል መልዕክት ያስተላለፉት ወ/ሮ ሰርካለም ወንድሙ ሳንቴ ሜዲካል ሴንተር ከዳሸን ባንክ ጋር ለረጅም ዓመታት ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰው ለወደፊትም ይበልጥ አብሮ ለመስራት ፍላጎትና እቅድ እንዳለው አመልክተዋል፡፡ ወ/ሮ ሰርካለም ለዳሸን ባንክ ደንበኞች፣ ሠራተኞች እና ባለአክሲዮኖች እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡ የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተወካይና የባንኩ ቺፍ ስትራቴጂ ኦፊሰር አቶ አየለ ተሸመ በበኩላቸው ዳሸን ባንክ ባለፉት 30 ዓመታት ያስመዘገበው ስኬት እንደ ሳንቴ ሚዲካል ሴንተር ያሉ ለረጅም ጊዜ አብረውት የሰሩ ደንበኞቹ ጭምር መሆኑን ጠቁመው ባንኩ ከመሰል ተቋማት ጋር ያለውን የስራ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰራም አመልክተዋል፡፡ ሳንቴ ሜዲካል ሴንተር የዳሸን ባንክን 30ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ መልዕክት በማስተላለፉም ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ዳሸን ባንክ የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመት ካለፈው ወር ጀምሮ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች እያከበረ ይገኛል፡፡ ❤ 17 👍 5 4 7.8K
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram