Dashen Bank @DashenBankEthiopia 16.03.2026 08:55 Скопировать Пожаловаться ዳሸን ባንክ በዲላ ከተማ ከደንበኞቹ ጋር የኢፍጣር ፕሮግራም አካሄደ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ የሚገኘውን የረመዳን ወር ምክንያት በማድረግ ዳሸን ባንክ በዲላ ከተማ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት (ሸሪክ) ደንበኞቹ ጋር የኢፍጣር ፕሮግራም አካሂዷል። በመርሃ-ግብሩ ላይ የዳሸን ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ አስናቀ ደምሴ እንደገለጹት፣ ፕሮግራሙ ባንኩ ያለውን ማኅበራዊ ተሳትፎ ለማጠናከር እና ከደንበኞቹ ጋር ያለውን መልካም ግንኙነት ለማሳደግ ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል። በፕሮግራሙ ላይ የዲላ ከተማ የዑለማዎች ምክር ቤት ሰብሳቢ ሼህ ሙሀመድ አሊይ፣ የከተማው ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው የባንኩ ደንበኞች ተገኝተዋል። የእለቱ ታዳሚዎች በተዘጋጀው ፕሮግራም ደስታቸውን በመግለጽ፣ በአብሮነት እንዲህ ባለ መልኩ ኢፍጣር ማካሄድ እምነቱ የሚያዘው ተግባር መሆኑን በመጥቀስ ለባንኩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ዳሸን ባንክ መሰል የኢፍጣር ፕሮግራሞችን በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች እያካሄደ ይገኛል። 👍 11 ❤ 6 6 7.2K
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram