Dashen Bank @DashenBankEthiopia 15.03.2026 18:55 Скопировать Пожаловаться ዳሽን ባንክ በሚዛን አማን ከተማ "ለእናቴ" በተሰኘው የረመዳን ሰደቃ መርሀ-ግብር ድጋፍ አደረገ የዳሽን ባንክ "ሸሪክ" ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የተከበረውን የረመዳን ወር ምክንያት በማድረግ፣ "ለእናቴ" በሚል መሪ ቃል ለአቅመ ደካማ እናቶች የማፍጠሪያ ድጋፍ አደረገ። በድጋፍ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የቤንች ሸኮ ዞን እስልምና ጉዳይ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሸህ አሊ ኡመር ባንኩ በኢኮኖሚ ዝቅተኛ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ ላሳየው ተነሳሽነት ምስጋና አቅርበዋል። ሸህ አሊ በንግግራቸው የረመዳን ወር የመረዳዳትና የእዝነት ወር በመሆኑ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም ግለሰቦች ለምስኪኖች የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው መቀጠል ይኖርባቸዋል ብለዋል። ሙስሊሙ ህብረተሰብ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎትን ለማግኘት ሲጠይቅ የነበረ ቢሆንም ዘርፉ ቀደም ሲል ብዙም ያልተስፋፋ እንደነበር አስታውሰው፤ ዳሽን ባንክ ለወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራ ያለው ስራ የሚያስመሰግን መሆኑንና ህብረተሰቡ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል። የዳሽን ባንክ የጅማ ዲስትሪክት ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ኤርያ ማኔጀር አቶ ጀሚል አብደላ ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል። የዳሽን ባንክ ደቡብ ምዕራብ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ሰላሙ አዴሎ በበኩላቸው፣ መረዳዳትና መተጋገዝ የባንኩ አንዱ እሴት መሆኑን ገልጸዋል። የረመዳን ፆም ወር በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመረዳዳትና በልግስና የሚታወቅ በመሆኑ፤ ዳሽን ባንክም ይህንኑ መንፈስ በመከተል ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል። ❤ 27 👍 9 2 4 7.9K
Обсуждение 2
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram