15.03.2026 14:04
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ "ቅድሚያ ለሴቶች" የሩጫ ውድድር 4ተኛ ሣምንት የልምምድ መርሃ-ግብር በወሎ ሰፈር ሠላም አደባባይ ተካሄደ

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከዳሸን ባንክ  ጋር በመተባበር የፊታችን መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም  ለሚያዘጋጁት
"ቅድሚያ ለሴቶች" የሩጫ ውድድር የልምምድ መርሃ-ግብር ተካሂዷል።

በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የኮምዩኒኬሽን ማኔጀር ሐና ገ/ስላሴ የዛሬው የልምምድ መርሃ-ግብር ተሳታፊዎች ለዋናው የሩጫ ውድድር ራሳቸውን የሚፈትሹበት እና የአብሮነት ጊዜ የሚያሳልፉት ነው ብለዋል።

ዳሸን ባንክ እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጠንካራ ትብብር እንዳላቸው ያነሱት ሐና፤ ባንኩ  ከምዝገባ ጀምሮ እስከ ሩጫ ድረስ ያሉ ኹነቶችን በማሳለጥ ከፍ ያለ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ብለዋል።

በዳሸን ባንክ ሔድ ሴልስ ወ/ሮ እስከዳር አሊ በበኩላቸው ዳሸን ባንክ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በመሆን በስፖርት ዘርፍ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በዛሬው ዕለት የተከናወነው የልምምድ ዝግጅት ተሳታፊዎች ለዋናው የሩጫ ውድድር ራሳቸውን የሚፈትሹበት እንደሆነም አመላክተዋል።

የልምምዱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ልምምዱ "ደስ እያለን የምናሳልፈውና ጤናችንን ለመጠበቅ የሚረዳን ነው" ብለዋል።
11
👍 2
5 6 7.9K

Обсуждение 5

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Dashen Bank

88.6K
Dashen Bank is one of the leading banks in Ethiopia with over 900+ branches and banking outlets.
Visit our official facebook* site @ https://www.facebook*.com/DashenBankOfficial
Visit our Website:https://dashenbanksc.com
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram