Dashen Bank @DashenBankEthiopia 15.03.2026 10:35 Скопировать Пожаловаться ዳሸን ባንክ በአዳማ ከተማ ከወለድ ነጻ የባንክ አግልግሎት (ሸሪክ) ደንበኞቹ የኢፍጣር መርሃ-ግብር አዘጋጀ የዳሸን ባንክ አዳማ ቀጠና ጽ/ቤት ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት (ሸሪክ) ደንበኞች በአዳማ ከተማ የኢፍጣር መርሃ-ግብር አከናውኗል። በአዳማ በተዘጋጀው በዚህ ዝግጅት ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት በዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት የኤም ኤስ ኤምኢ እና አጄንሲ ባንኪንግ ዳይሬክተር አቶ ዴታሞ ሬድዋን ደንበኞችን "ከእናንተ ጋር በመስራታችን ትልቅ አክብሮት አለን" ብለዋል። በመርሀ-ግብሩ ላይ የአዳማ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክትል ስራ አስኪያጅ ሸህ ሑሴን አህመድ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም ተሳታፊ ሆነዋል። የሸሪክ ደንበኞች ለተደረገላቸው የኢፍጣር መርሀ-ግብር ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ዳሸን ባንክ ታላቁን የረመዳን ወር ምክንያት በማድረግ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የኢፍጣር ዝግጅት እያከናወነ ይገኛል። 👍 17 ❤ 7 12 8 8.5K
Обсуждение 12
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram