Bunna Bank @BunnaBankOfficial 08.04.2026 12:13 Скопировать Пожаловаться ቡና ባንክ ለዳሸን ባንክ 30ኛ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ ቡና ባንክ ዳሸን ባንክ የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በዳሸን ባንክ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡ በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የቡና ባንክ ቺፍ ስትራቴጂ እና ፓርትነርሺፕ ኦፊሰር አቶ ሙሉነህ አያሌዉ ባደረጉት የእንኳን አደረሳችሁ ንግግር “ዳሸን ባንክ ባለፉት 30 ዓመታት በባንክ ኢንዱስትሪው የፈጠረው መልካም ስም እና ስኬት ተጠናክሮ እንዲቀጥል መልካም ምኞታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡ አቶ ሙሉነህ በዚሁ የእንኳን አደረሳችሁ ንግግራቸው እንዳሉት ኢንደስትሪው ከፉክክር ወደ ትብብር በሚያመዝን አሰራር መጓዙ ለሃገሪቱ የፋይናንስ ኢንደስትሪ እድገት ጠቃሚ መሆኑን ገልጸው በሁለቱ ባንኮች መካከል በጋራ ለመስራት የሚያግዙ የትብብር ዘርፎች የሚኖሩበት አማራጭ ሰፊ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ የባንኩ ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽንስ ዳይሬክተር አቶ መላኩ ብርሃኑ በበኩላቸው ባደረጉት የእንኳን አደረሳችሁ ንግግር ዳሽን ባንክ በተለይ የወጣቶችን ስራ ፈጠራ ለማሳደግ እያከናወነ ያለውን የድጋፍና ማህበራዊ ሃላፊነት ተግባር አድንቀዋል፡፡ ሁለቱ ባንኮች ዳሸን እና ቡና የሚል መጠሪያቸውን ሃገርበቀል ከሆኑት ብርቅዬ ሃብቶቻችን ላይ መውሰዳቸው ተመሳሳይ ያደርጋቸዋል ያሉት አቶ መላኩ ይህ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሃብትነታቸውን የሚያረጋግጥ ስያሜያቸው በትብብር ለመስራት አንድ በር የሚከፍት አጋጣሚ ነው ብለዋል፡፡ የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተወካይና የባንኩ ቺፍ ስትራቴጂ ኦፊሰር አቶ አየለ ተሾመ በበኩላቸው ቡና ባንክ ለዳሽን ባንክ 30ኛ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በማቅረቡ በባንኩ ከፍተኛ አመራሮች ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ አቶ አየለ እንዳሉት የውጭ ባንኮች ወደሃገር ውስጥ መግባት የሚችሉበት እድል ከመከፈቱ ጋር በተያያዘ መጪው ጊዜ በአገር በቀል ባንኮች መካከል ያለው ትብብር ከፍ ሊል የሚገባበት ወቅት መሆኑን ገልጸው በሁለቱ ባንኮች መካከልም ይኸው ተፈጻሚ የሚሆንበት እድል ከፍ ያለ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የዳሽን ባንክ ከፍተኛ የስራ አመራር አባላት ለቡና ባንክ አመራሮች የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል በማድረግ በሁለቱ ባንኮች ብራንድ የተሰራ የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞት መግለጫ ኬክ በሁለቱም ባንኮች አመራር አባላት በጋራ ተቆርሷል፡፡ ❤ 41 👍 13 👎 3 🤡 3 😁 2 2 9 10.2K
Обсуждение 2
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram