Bunna Bank @BunnaBankOfficial 16.03.2026 12:21 Скопировать Пожаловаться Bunna Bank Фото: Медиафайл ቡና ባንክ ለቢላሉል ሀበሺ ማዕከል የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ ቡና ባንክ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣትና ከማህበረሰቡ ጋር ያለውን ስትራቴጂያዊ ትስስር ለማጠናከር በማለም፤ በቢላሉል ሀበሺ የታሪክና የሰብአዊ ድጋፍ ማዕከል ልዩ የጉብኝትና የድጋፍ መርሃ ግብር አከናወነ። በባንኩ የፋይናንስና የኮርፖሬት አገልግሎት ቺፍ ኦፊሰር አቶ ለውጤ ጥሩሰው የተመራው የባንኩ አመራሮች ልዑክ፤ በማዕከሉ የሚገኙትን የቢላሉል ሀበሺ ሙዚየም እንዲሁም የአልባሳት፣ የጫማና የቆዳ ውጤቶች ማምረቻና ማሰልጠኛ ማዕከልን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። አቶ ለውጤ በማዕከሉ ባደረጉት ምልከታ የተሰማቸውን ጥልቅ አድናቆት ገልጸዋል። ማዕከሉ የሀገሪቱን ታሪክና ቅርስ ከመጠበቅ ባለፈ፤ ወገኖችን በክህሎት በማብቃትና የቲሞችንና ደጋፊ ያጡ ወገኖችን በመደገፍ ረገድ ከውልደት እስከ እረፍት ያለውን የሰው ልጅ የሕይወት ጉዞ መሠረት አድርጎ የሚያከናውናቸው ተግባራት እጅግ አስደናቂ መሆናቸውን ጠቁመዋል። አቶ ለውጤ አያይዘውም ባንኩ ለእንዲህ አይነት የሰብአዊ ልማት ስራዎች ያለውን ዝግጁነት ገልጸዋል። ባንኩ በኻዲም ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎቱ አማካኝነት የቁጠባና የፋይናንስ አገልግሎት እንዲሁም ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የዲጂታል ፋይናንስ (DFS) ብድሮችን እያቀረበ መሆኑን አስረድተዋል። "ማዕከሉ እያከናወነ ያለው የልማትና የክህሎት ስራ ባንኩ ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ካዘጋጀው የፋይናንስ ድጋፍ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው" ያሉት አቶ ለውጤ፤ ባንኩ ዛሬ ለቢላሉል ሀበሺ የልማትና መረዳጃ ዕድር ያደረገው ድጋፍ መጀመሪያ መሆኑንና ወደፊትም ይህ አጋርነት ይበልጥ በሰፊው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። የማዕከሉ አስተዳዳሪዎች በበኩላቸው፤ ቡና ባንክ ለታሪክና ለሰብአዊ ስራዎች የሰጠውን ትኩረት አድንቀዋል። እንዲህ ያሉ ትልልቅ የፋይናንስ ተቋማት ወደ ማዕከሉ መጥተው አጋርነታቸውን ማሳየታቸው፤ ማዕከሉ የሀገሪቱን ድንቅ ቅርሶች ለመጠበቅና ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ለመድረስ ለሚያደርገው ጥረት ትልቅ አቅም እንደሚሆን ገልጸዋል። በተያያዘም ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን የመወጣት ተግባር አድማሱን በማስፋት፤ በደብረ ብርሃን/ሸዋ ሮቢት፣ በጅማ፣ በሐዋሳ እንዲሁም በአዲስ አበባ ደቡብ ዲስትሪክት ስር ለሚገኙ አቅመ ደካማ ነዋሪዎች የሰደቃ (የድጋፍ) መርሃ ግብር አከናውኗል። በእነዚህ አካባቢዎች የሚገኙ የባንኩ የዲስትሪክት አመራሮችና ሰራተኞች በመገኘት፣ ለተቸገሩ ወገኖች አስፈላጊውን ድጋፍ አበርክተዋል። ይህም ድጋፍ ነዋሪዎቹ የረመዷንን ወር በደስታና በሰላም እንዲያሳልፉ ለማገዝ የታለመ ነው። የባለራዕዮች ባንክ የሆነው ቡና ባንክ ማህበረሰቡን የሚያሳትፉ መሰል በጎ ተግባራትን አቅም በፈቀደ መጠን ማከናወኑን አጠናክሮ ይቀጥላል። ❤ 48 👍 19 🙏 6 👏 5 6 7 20.1K
Обсуждение 6
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram