09.03.2026 16:16
ቡና ባንክ በባህር ዳር ለሚገኙ ወገኖች የሰደቃ ድጋፍ አደረገ

የቡና ባንክ ባህር ዳር ዲስትሪክት ታላቁን የረመዷን ወር ምክንያት በማድረግ፣ በዲስትሪክቱ ዙሪያ ለሚገኙ አቅመ ደካማ ነዋሪዎች የሰደቃ (የድጋፍ) መርሃ ግብር አካሄደ።
ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ባለው ቁርጠኝነት መሰረት፣ የዲስትሪክቱ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት ለተቸገሩ ወገኖች አስፈላጊውን ድጋፍ አበርክቷል። ይህም ድጋፍ ነዋሪዎቹ የረመዷንን ወር በደስታና በሰላም እንዲያሳልፉ ለማገዝ የታለመ ነው።
ቡና ባንክ ከንግድ ስራው ጎን ለጎን ለማህበረሰቡ ደህንነት ትልቅ ቦታ የሚሰጥ ባንክ እንደመሆኑ፤ ይህ የሰደቃ ስነስርዓትም እንደሁልጊዜው ሁሉ ከህዝባችን ጋር ያለንን አጋርነት የምናሳይበት ነው ሲል ዲስትሪክቱ አስታውቋል።
የባለራዕዮች ባንክ የሆነው ቡና ባንክ ማህበረሰቡን የሚያሳትፉ መሰል በጎ ተግባራትን አቅም በፈቀደ መጠን ማከናወኑን አጠናክሮ ይቀጥላል።

ቡና ባንክ - የባለራዕዮች ባንክ!

#ቡናባንክ #ረመዷን_ከሪም #ባህርዳር #ሰደቃ #ኢትዮጵያ #BunnaBank #BahirDar #Ramadan2026
41
👏 15
😁 6
6 4 9.7K

Обсуждение 6

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Bunna Bank

34.4K
Welcome to the official Telegram channel of Bunna Bank S.C.
Here you will receive verified updates, announcements, and customer service information.
This channel is for informational purposes only.
Открыть в Telegram