Bunna Bank @BunnaBankOfficial 07.03.2026 14:14 Скопировать Пожаловаться ቡና ባንክ በመቄዶንያ ማዕከል የኢፍጣር ማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር አከናወነ። ቡና ባንክ ዓርብ የካቲት 27 ቀን 2018 ዓ.ም በመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በመገኘት ልዩ የኢፍጣር የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር አከናወነ። ማኅበራዊ ኃላፊነቱን የመወጣትና ከማህበረሰቡ ጋር ያለውን ትስስር የማጠናከር አካል በሆነው የረመዳን ኢፍጣር መርሃ ግብር ላይ የባንኩ የወለድ ነጻ ባንክ አገልግሎት አመራርና ሰራተኞች በማዕከሉ በአካል ተገኝተው የሰብአዊ ድጋፍ ስራዎችን የጎበኙ ሲሆን፣ ከነዋሪዎቹ ጋርም የኢፍጣር ማዕድ በመጋራት ልዩ የአብሮነት ጊዜን አሳልፈዋል። ይህንኑ በጎ ተግባር አስመልክተው የባንኩ የወለድ ነፃ ባንክ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ሙሐመድ ናስር “ እርጅና እና ህመም በማንኛውም ሰው ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ የሕይወት ገጠመኞች በመሆናቸው በእነዚህ አስቸጋሪ ጊዜያት መጠለያና እንክብካቤ ላጡ ወገኖች መድረስ የሁላችንም ሰብዓዊ ግዴታ ነው” ብለዋል። ይህ ተግባር ቡና ባንክ ከትርፍ ባሻገር ለሰው ልጅ ክብርና ደህንነት ቅድሚያ እንደሚሰጥ በተግባር ማሳያ መሆኑን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ፣ በተለይም የረመዳን ወር የመረዳዳትና የመተሳሰብ ወቅት መሆኑ ለጉብኝቱ ልዩ ትርጉም እንደሚሰጠው አስረድተዋል። ይህ የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ባንኩ በቅርቡ ባደረገው የስትራቴጂ ክለሳ ልዩ ትኩረት ለሰጠው "ኻዲም" ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ጋርም የተቆራኘ ነው። "አገልጋይ" የሚል ትርጉም ያለው ይህ "ኻዲም" የተሰኘው አገልግሎት፤ ደንበኞችን በታማኝነት ከማገልገል ባለፈ እንደ መቄዶንያ ያሉ ተጋላጭ ወገኖችን የሚረዱ ተቋማትን መደገፍ አንዱ መገለጫው ነው። በአሁኑ ወቅት ከ600 ሺሕ በላይ ደንበኞችን ያፈራው ይህ አገልግሎት፣ በሁሉም 444 የባንኩ ቅርንጫፎች በመስኮት ደረጃ እንዲሁም በአምስት ልዩ ቅርንጫፎች ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። በመጨረሻም፣ በአሁኑ ወቅት ከ8,500 በላይ ተንከባካቢ የሌላቸው ወገኖችን እየረዳ የሚገኘው የመቄዶንያ ማዕከል ነዋሪዎችና አስተባባሪዎች፤ ቡና ባንክ ላሳየው አጋርነትና ላደረገው ድጋፍ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። እንዲህ ያሉ ግዙፍ ተቋማት ወደ ማዕከሉ መጥተው ከነዋሪዎች ጋር ጊዜ ማሳለፋቸው ለሰብአዊ ስራቸው ትልቅ የሞራል ጥንካሬ እንደሚሰጣቸውም ገልጸዋል። መርሃ ግብሩ በጋራ የኢፍጣር ስነ-ስርዓትና በምስጋናና ምርቃት የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ባንኩ መሰል ማህበረሰብ ተኮር ተግባራትን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል። ❤ 33 👍 14 👏 5 1 6 11K
Обсуждение 1
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram