05.03.2026 17:02
ቡና ባንክ የደንበኞች ግንኙነቱን የሚያጠናክር የረመዳን የኢፍጣር መርሃ ግብር አካሄደ

ቡና ባንክ ከደንበኞቹ ጋር ያለውን ትስስር ይበልጥ ለማጥበቅ ያለመ ልዩ የረመዳን የኢፍጣር መርሃ ግብር ረቡዕ የካቲት 25 ቀን 2018 ዓ.ም በሀይሌ ግራንድ ሆቴል በድምቀት አከናወነ።

በዚህ ልዩ መርሃ ግብር ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማ ጉባዔ ጽ/ቤት ኃላፊ ሸህ ሙሐመድ-ዘይን ዘህረዲንን ጨምሮ ሌሎች የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ አመራሮች፣ የባንኩ ደንበኞች፣ እንዲሁም የተለያዩ አጋር አካላት ተገኝተው የኢፍጣር የአብሮነት ጊዜን በጋራ አሳልፈዋል።

በዚህም የባንኩ ኻዲም ከወለድ ነጻ አገልግሎት የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ አባላትን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከተጋባዦቹ ጋር ተገናኝተው የጋራ ቆይታ አድርገዋል። ይህ መድረክ አመራሩ ከደንበኞችና ከኃይማኖት አባቶች ጋር የጠበቀ ትስስር እንዲፈጥር፣ ፍላጎቶቻቸውን በቅርበት እንዲረዳና ተቋሙ ከፋይናንስ አገልግሎት ባለፈ ያለውን አጋርነት እንዲያረጋግጥ ምቹ አጋጣሚን ፈጥሯል።

የቡና ባንክ ቺፍ ሪቴልና ቅርንጫፍ ባንኪንግ ኦፊሰር አቶ እስክንድር ዲበኩሉ በዝግጅቱ ላይ ባስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት እንዳስታወቁት፤ ቡና ባንክ በቅርቡ ባደረገው የሥትራቴጂ ክለሳ ለኻዲም ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ትልቅ ትኩረት እንደተሰጠው አንስተዋል። ባንኩ በዚህ ረገድ የደንበኞቹን ፍላጎት ለማርካት ሰፊ ስራዎችን እየሰራ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

መርሃ ግብሩ የረመዳንን ወር እሴቶች ከማክበር ባለፈ በባንኩ አገልግሎት ተደራሽነት፣ በቀጣይ በሚኖራቸው የስራ ግንኙነት ዙሪያ ከአመራሩ ጋር ሀሳብ ለመለዋወጥ ዕድልን የፈጠረ ነበር። በዚህም በዝግጅቱ የታደሙት የእስልምና ጉዳዮች አመራሮችና ደንበኞች ባንኩ ላሳየው ተነሳሽነት ምስጋናቸውን አቅርበው፣ እንዲህ ያለው የፊት ለፊት ግንኙነት መተማመንን ለመገንባትና ባንኩ በቀጣይ ለሚቀርጻቸው ስራዎች ጠቃሚ ግብዓቶችን ለማግኘት የራሱን ሚና እንደሚጫወት ጠቅሰው ባንኩ በኻዲም ከወለድ ነጻ አገልግሎት በኩል የጀመረውን ስራ ከዚህ የበለጠ አጠናክሮ እንዲቀጥል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በመጨረሻም መርሃ ግብሩ በኢፍጣር ማዕድ መጋራትና በጋራ የምስጋናና ጸሎት ስነ-ስርዓት የተጠናቀቀ ሲሆን፣ የኢፍጣር ዝግጅቱ ቡና ባንክ አካታችነትንና ቀጥተኛ ተሳትፎን ቅድሚያ በመስጠት ለደንበኞቹ እሴቶች ያለውን አክብሮትና ለአብሮነት ልዩ ትኩረት የሚሰጥ ተቋም መሆኑን ያሳየበት አንዱ መድረክ ሆኖ አልፏል።
61
👍 18
🙏 15
35 39 14.8K

Обсуждение 35

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Bunna Bank

34.4K
Welcome to the official Telegram channel of Bunna Bank S.C.
Here you will receive verified updates, announcements, and customer service information.
This channel is for informational purposes only.
Открыть в Telegram