avatar
Amhara Media Corporation
@AmharaMassMedia
10.04.2026 11:52
"በዓለ ስቅለትን ስናከብር ከእውነት ጋር በመቆም ይሁን" ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
ባሕር ዳር፡ ሚያዚያ 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ስቅለት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። መልእክታቸው እንደሚከተለው ቀርቧል፦
ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ስቅለት እንኳን አደረሳችሁ።
ዕለቱ የዓለምን በደል ሊሽር፤ የአዳምን ዕዳ ሊክስ መድኃኔዓለም የተሰቀለበት ዕለት ነው። ይህ ቀን መንጋነት ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ የተማርንበትም ነው። ጲላጦስ በኢየሱስ ላይ አንዳች ነገር አላገኘበትም። የተሰበሰበው መንጋ ግን እውነትን መቀበል አልፈለገም። ስለዚህ "ስቀለው፤ አስወግደው " ብሎ በጅምላ ፈረደ።
በጅምላ ፍርድ የተነሳ እውነት በመረጃና ማስረጃ መወሰኑ ቀርቶ በጩኸት ተወሰነ። ጥቂቶች እውነተኞች ብቻ ከእውነት ጋር ቆሙ። ብዙዎቹ ግን በአፈ ቀላጤዎች ተታልለው ስሜታቸውን ተከተሉ። በዚህ የተነሣ በንጹሕ ላይ ተፈረደ። የሚሞተው ተለቅቆ፣ የማይሞተው ሞተ። ሐሰት ቀን ወጥቶለት፣ እውነት ተሰቀለ።
ይሄንን ቀን ስናከብር ከእውነት ጋር በመቆምና መንጋነትን በመጸየፍ ይሁን።
መልካም በዓል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
������
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
5
1.3K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Amhara Media Corporation

48.7K
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
Открыть в Telegram