\በአፋር ክልል በሰመራ ሎጊያ ከተማ ሀገራዊ ለውጡን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአፋር ክልል ሰመራ ሎጊያ ከተማ በሀገራዊ ለውጡ የተመዘገቡ የልማት ድሎችን ዕውቅና የሚሰጥ እና አጋርነትን የሚገልጽ ደማቅ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
ሠልፈኞቹ የኢትዮጵያ ከፍታ በእጃችን ነው፤ መጋቢት የፅናት መለኪያ የፈተና መሻገሪያ ነው፤ መሰረት ባለው እርምጃ ወደ ተምሳሌት ሀገርነት የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።
ከአፋር ክልል ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ባለፉት ስምንት ዓመታት በክልሉም ኾነ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተመዘገቡ የልማት እና የመሠረተ ልማት ግንባታዎች የለውጡ ፍሬዎች መኾናቸውን ተናግረዋል።
የተጀመረው የብልጽግና ጉዞ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ አስታውቀዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
������
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram