avatar
Amhara Media Corporation
@AmharaMassMedia
08.04.2026 11:37
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተጠባቂ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ዛሬ ከሚደረጉ ተጠባቂ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች መካከል ፔኤስጂ ከሊቨርፑል የሚያደርጉት ጨዋታ አንደኛው ነው።
በደካማ አቋም ላይ የሚገኘው ሊቨርፑል ዛሬ በፓሪስ ብርቱ ፈተና ይገጥመዋል። የባለፈው ዓመት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው ፔኤስጂ ዘንድሮስ ስኬታማ ጉዞ ያደርግ ይኾን ? የሚለው ይጠበቃል።
የሊቨርፑሉ የአጥቂው አሌክሳንደር ኢሳቅ ከረጅም ጊዜ ጉዳት በኋላ ወደ ልምምድ ተመልሷል። በዛሬው ጨዋታም የስብስቡ አካል እንደሚኾን ይጠበቃል። ጨዋታው ምሽት 4:00 ይካሄዳል።
በሌላ ጨዋታ የስፔኖቹ ባርሴሎና እና አትሌቲኮ ማድሪድ ይገናኛሉ። ባለፈው ቅዳሜ በስፔን ላሊጋ ተገናኝተው የነበሩት ሁለቱ ክለቦች ከቀናት በኋላ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ይገናኛሉ።
ከፍተኛ ትንቅንቅ እንደሚካሄድበት የሚጠበቀው ይህ ጨዋታ ምሽት 4:00 ይካሄዳል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
������
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
5
1.9K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Amhara Media Corporation

48.7K
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
Открыть в Telegram