avatar
Amhara Media Corporation
@AmharaMassMedia
06.04.2026 14:10
በአፋር ክልል አይሳኢታ ከተማ የለውጡን ጉዞ የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

ባሕር ዳር: መጋቢት 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ)በአፋር ክልል በአይሳኢታ ከተማ መጋቢት 24/ 2010 ዓ.ም የመጣውን ሀገራዊ ለውጥ ተከትሎ የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠል እና የለውጥ ጉዞውን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም ያለመ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።

ሰልፉ ባለፉት ዓመታት የተገኙ ፖለቲካዊ ፤ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ድሎችን እውቅና በመስጠት በክልሉ የሚታየውን ልማት እና ሰላም ይበልጥ ለማሳደግ ያለመ መኾኑ ተገልጿል።

​ሰልፈኞቹ የለውጥ ሂደቱ በክልሉ መረጋጋትን እና ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ከማረጋገጡም ባለፈ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን በማጠናከር ጉልህ ሚና ተጫውቷል ብለዋል።

የለውጥ ሂደቱን ከማንኛውም እንቅፋት በመጠበቅ እና ለመንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ በመስጠት የጀመሩትን የልማት ሥራዎች ለማስቀጠል ዝግጁ መኾናቸውን ተናግረዋል።

​ይህ የድጋፍ ሰልፍ በክልሉ ሰፊ ተቀባይነት እያገኘ የመጣውን የለውጥ አስተሳሰብ የሚያንጸባርቅ ነው ተብሏል። የኢትዮጵያን አንድነት እና የብልጽግና ጉዞ ለማሳካት ያላቸውን የማይናወጥ አቋም ማንጸባረቃቸው ተገልጿል።

ከአፋር ክልል ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ሕዝቡ ለለውጡ እያሳየ ያለው ወገንተኝነት ለቀጣይ ሥራዎች ትልቅ አቅም እንደሚኾን ተመላክቷል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
������
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
👍 6
3.2K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Amhara Media Corporation

48.7K
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
Открыть в Telegram