avatar
Amhara Media Corporation
@AmharaMassMedia
04.04.2026 18:56
"ኢትዮጵያን የሚመጥን ከተማ ለመገንባት እየሠራን ነው" ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 26/2018 ዓ.ም(አሚኮ) በባሕር ዳር ከተማ በአጼ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ ከፓፒረስ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ እስከ ዲያስፖራ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚዘልቅ የ3 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ እና የኮሪደር ልማት ሥራ ተጀምሯል።

በማስጀመሪያው ላይ የተገኙት የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የኮሪደር ልማት "ኢትዮጵያን የሚመጥን ከተማ ለመገንባት" የሚያስችል መኾኑን ተናግረዋል።

ርእሰ መሥተዳድሩ ሥራው ዜጎች በንጹህ አካባቢ የመኖር መብታቸውን የሚያረጋግጥ መኾኑንም ገልጸዋል።

የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ልማቱ የከተማዋን ኢኮኖሚ እንደሚያነቃቃ እና የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት እንደሚያረጋግጥ ተናግረዋል።

ልማቱ ዘመናዊ የከተማ ገጽታ ከመፍጠር ባለፈ ለእግረኞች ደኅንነት እና ለነዋሪዎች ምቹ አየር እንዲኖር ያስችላል ተብሏል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
������
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
👍 5
1
1 1 2.8K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Amhara Media Corporation

48.7K
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
Открыть в Telegram