avatar
Amhara Media Corporation
@AmharaMassMedia
03.04.2026 19:02
በገና የባሕል ስፖርት ውድድር አማራ ክልል አሸናፊ ኾነ።

ባሕር ዳር: መጋቢት 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ​በ23ኛው የኢትዮጵያ ባሕል ስፖርቶች እና በ19ኛው የባሕል ፌስቲቫል የገና ስፖርት ፍፃሜውን አግኝቷል።

ውድድሩ ላይ አራት ተሳታፊዎች ለአሸናፊነት በዙር ተጫውተዋል።

ዛሬ ሦሥተኛ ጨዋታዎች ሲደረጉ አማራ ክልል አዲስ አበባን 2ለ1 አሸንፏል።

ይህ ድል አማራ ክልል በሰባት ነጥብ በገና ስፖርት አጠቃላይ አሸናፊ አድርጎታል።

ሀረሪ ክልልን 6ለ0 ያሸነፈው ኦሮሚያ ክልል ሁለተኛ ኾኖ ውድድሩን ጨርሷል።

አንድ ጨዋታ አሸንፎ፣ በአንዱ አቻ የተለያየው እና በአንዱ የተሸነፈው አዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ደግሞ ሦሥተኛ ኾኖ ውድድሩን አጠናቅቋል።

ዘጋቢ፦ ኃይሉ አዳነ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
������
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
3
👍 1
👏 1
2 2.4K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Amhara Media Corporation

48.7K
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
Открыть в Telegram