avatar
telebirr
@telebirr
04.04.2026 21:03
ኢትዮ ቴሌኮም የገባውን ቃል በተግባር በማረጋገጥ ለደንበኞቹ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በሽልማት አበረከተ!

ኢትዮ ቴሌኮም 130ኛ ዓመት ክብረ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከመስከረም 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለደንበኞቹ ባዘጋጀው የኢትዮ 130 ሜጋ ፕሮሞ እና ኢትዮ 131 ላኪ ስሎት የሽልማት መርሃ ግብር ለዕድለኞች ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ሲያበረክት መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ክብረ በዓሉን ምክንያት በማድረግ እስካሁን 6 የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ጅማና ወሊሶ ባለዕድለኛ ደንበኞቻችን እንዲሁም 13 ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎችን ለአርባምንጭ፣ ሐረር፣ አርሲ ነጌሌ፣ አዲስ አበባ፣ ሆሳዕና፣ አዳማ፣ ሐዋሳ፣ ወልቂጤ እና ቦንጋ ዕድለኞች ቁልፍ ማስረከቡ ይታወሳል፡፡

በተጨማሪም 422 ዘመናዊ ስማርት ስልኮችን፣ ለ4,405 ደንበኞቻችን በየቀኑ እና በየሳምንቱ በድምሩ 46 ሚሊዮን ብር የቴሌብር ኤሌክትሮኒክ ገንዘብ እንዲሁም ከ2.7 ሚሊዮን በላይ የሞባይል ጥቅሎችን ጨምሮ፣ ከ143 ሚሊዮን ብር በላይ አጠቃላይ ዋጋ ያላቸውን ሽልማቶች አበርክቷል።

በትላንትናውና በዛሬው ዕለትም ዕጣ ለወጣላቸው የአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ጅማ እና የአሶሳ ባለዕድለኞች፣ ሦስት ዘመናዊ ቮልስዋገን (ID.4)፣ ሁለት የቢ.ዋይ.ዲ (BYD) እና አንድ ቶዮታ (BZ3x) የኤሌክትሪክ መኪኖችን የኩባንያችን ከፍተኛ አመራሮች፣ የሚዲያ አጋሮቻችንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ቃል በገባው መሠረት በመሸለም ቁልፍ አስረክቧል፡፡

ኩባንያችን ደንበኞቹን ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ከመሸለም ባሻገር፣ ለኢትዮጵያ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ኢኒሼቲቭ ስኬትም የራሱን የላቀ ሚና በመወጣት ላይ ይገኛል።

#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #RealizingDigitalEthiopia
46
👍 15
😁 7
🙏 4
👌 3
🤩 1
3 12.1K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram
Открыть в Telegram