avatar
telebirr
@telebirr
03.04.2026 23:42
ኩባንያችን አራተኛውን የህዝብ ኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ ጣቢያ በአዳማ ይፋ አደረገ

ኩባንያችን ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ ውጪ በአዳማ ከተማ ይፋ ያደረገው የህዝብ የኤሌክትሪክ መኪና መሙያ ጣቢያ በአንድ ጊዜ 12 እጅግ በጣም ፈጣን መሙያዎችን ያካተተ ሲሆን፣ ይህም ያሉንን ጣቢያዎች የማስተናገድ አቅም በእጅጉ ከፍ ለማድረግ ያስችላል፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚያችን “ከአራቱ ጣቢያዎች በተጨማሪ ለተለያዩ ቁልፍ ሀገራዊ ተቋማት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ኃይል መሙያ መሠረተ-ልማቶችን በመገንባት ላይ እንገኛለን ያሉ ሲሆን፣ ይህም የሀገራችን አረንጓዴ ልማት ሥነ-ምህዳርን ለመደገፍ ያለንን ጽኑ ቁርጠኝነት ያሳያል” ብለዋል፡፡

አክለውም “ሀገራችን ወደ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ፣ ዘላቂ የትራንስፖርት አማራጮች እና ዲጂታል ኢኖቬሽን የምታደርገውን ሽግግር እያፋጠነች ባለችበት በዚህ ወቅት፣ እነዚህን የኤሌክትሪክ ኃይል መሙያ ጣቢያዎች በአጭር ጊዜ ገንብተን ስራ ላይ እንዲውሉ አድርገናል” ብለዋል፡፡

ኩባንያችን ቀደም ሲል በአንድ ጊዜ 48 መኪኖችን ማስተናገድ የሚችሉ ጣቢያዎችን ወደ ስራ ያስገባ ሲሆን፣ ከየካቲት 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከ284 ሺህ በላይ የኤሌክትሪክ መኪኖች፣ 7,159,066.88 ኪሎዋት ኃይል መሙላት ችሏል፡፡

ይህም 10,028,363.32 ኪ.ግ ካርቦን ዳይኦክሳይድ ወደ ከባቢ አየር እንዳይለቀቅ ማድረግ የቻለ ሲሆን፣ ከ49,559 በላይ ዛፎችን ከመትከል ጋር ይነጻጸራል።

በተጨማሪም ሌሎች ባለድርሻ አካላት የገነቧቸው ጣቢያዎች በተቀናጀ የዲጂታል ስነ-ምህዳር ውስጥ እንዲካተቱ የሚያስችል ሀገር አቀፍ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ኃይል መሙያ ፕላትፎርም ያዘጋጀ ሲሆን፣ ይህም ተጠቃሚዎቻቸው ሁሉን አቀፍ የዲጂታል አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል፡፡

ለበለጠ መረጃ ፡ https://bit.ly/4mePALQ
44
👍 16
🙏 12
😢 2
14.6K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram
Открыть в Telegram