avatar
telebirr
@telebirr
31.03.2026 23:42
ኢትዮ ቴሌኮም ዜጎች ካሉበት ሆነው የሰነድ ማረጋገጥ፣ የውክልና ስልጣን እና የጠበቃ ፈቃድ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል "ቴሌሳይን" የተሰኘ ሶሉሽን በይፋ አስመረቀ!

ኢትዮ ቴሌኮም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከፍትህ ሚኒስቴር እና ከፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር በአጋርነት፤ የሰነድ ማረጋገጥ፣ የውክልና ስልጣን እና የጠበቃ ፈቃድ መስጠትና ማደስ የሚያስችለውን "ቴሌሳይን" (teleSign) የተሰኘ ሶሉሽን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

ቴሌሳይን በዲጂታል መንገድ የዲያስፖራው ማህበረሰብም ሆነ በሀገር ውስጥ የሚገኙ ዜጎች በአካል ኤምባሲ/የቆንስላ ጽ/ቤት ወይም በተቋማት ቢሮ ሳይገኙ የውክልና ስልጣን ለመስጠትም ሆነ ለማንሳት ያስችላል።

በተጨማሪም ድርጅቶችና ዜጎች ማንኛውንም ህጋዊ ሰነድ ካሉበት ቦታ ሆነው በዲጂታል መንገድ እንዲያረጋግጡ እንዲሁም የህግ ባለሙያዎችም የጠበቃ ፈቃድ ለማውጣትና ለማደስ የሚያስችል አሠራርን ያካተተ ነው፡፡

ይህ ሶሉሽን በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የታገዘ የቪዲዮ ማንነት ማረጋገጫን (Liveness Detection) እና ከፋይዳ ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ጋር የተቀናጀ የማንነት ማረጋገጫ ስርዓትን የሚጠቀም በመሆኑ አስተማማኝነቱ የተረጋገጠ ነው።

ሶሉሽኑ ቀደም ሲል ሳምንታትን ይፈጅ የነበረውን አሠራር ወደ ጥቂት ደቂቃዎች ዝቅ ያደረገ ሲሆን፤ ተገልጋዮች ክፍያን በቴሌብር በመፈጸም አገልግሎቱን በማንኛውም ሰዓት ማግኘት ይችላሉ።

የዜጎችና የተቋማት መረጃዎች በቴሌ የክላውድ መሰረተ-ልማት ላይ ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲቀመጥ በማድረግ ሀገራዊ የመረጃ ሉዓላዊነትን ያረጋግጣል።

ተገልጋዮች በ teleSign የሞባይል መተግበሪያ ወይም በድረ-ገጽ ካሉበት ቦታ ሆነው አገልግሎቶችን ማግኘት ይችላሉ።

ለበለጠ፡ https://bit.ly/4s7BJbp
59
🙏 11
👍 10
😁 7
😢 2
👌 2
👏 1
15 19.1K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram
Открыть в Telegram