telebirr @telebirr 26.03.2026 23:44 Скопировать Пожаловаться ኢትዮ ቴሌኮም እና የጣሊያኑ አስኮት ኢነርጂ አረንጓዴ ዲጂታል መሠረተ ልማት ለመገንባት ያለመ ስትራቴጂካዊ ውይይት አካሄዱ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ በጋታኖ ፋሲያና ከተመራ የአስኮት ኢነርጂ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጋር በአገር አቀፍ የመሠረተ ልማት ግንባታ ላይ የታዳሽ የኃይል ቴክኖሎጂዎችን ለማስፋፋት ያለመ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል። ይህም የኩባንያውን “ቀጣዩ አድማስ፡ ዲጂታል እና ከዚያም ባሻገር 2028” ስትራቴጂ ከማሳካት ባለፈ፣ ፈጣን የቴክኖሎጂ ሽግግርን የካርቦን ልቀትን ከሚቀንስ ዘላቂ ልማት ጋር በማጣጣም ረገድ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል። ክብርት ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንደገለጹት፤ ለዲጂታል መሠረተ ልማት ዘላቂነት የአረንጓዴ እና ታዳሽ የኃይል አቅርቦት መገንባት ወሳኝ ነው። አክለውም የኃይል አጠቃቀምን ማሻሻል እና ታዳሽ አማራጮችን መጠቀም ለሥራ ማስኬጃ ወጪ ቁጠባ፣ ለአገልግሎት ዋጋ ተመጣጣኝነት እና ለዘላቂ ተቋም ግንባታ ቁልፍ መሆኑንም አብራርተዋል። የአስኮት ኢነርጂ ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው፤ ኩባንያቸው የነዳጅ ፍጆታን በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንሱ እና የመሠረተ ልማት ጣቢያዎችን የኃይል ፍላጎት በዘላቂነት የሚያሟሉ ዘመናዊ የሃይብሪድ ኢነርጂ ቴክኖሎጂዎችን በማቅረብ የሚታወቅ መሆኑን በማብራራት፤ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ለመሥራት ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል። በመጨረሻም ሁለቱ ኩባንያዎች የቀረቡትን የቴክኖሎጂ መፍትሔዎች ወደ ተግባር የሚለውጥ የጋራ የቴክኒክ ቡድን ያቋቋሙ ሲሆን፤ የፋይናንስ ምንጮችንም በጋራ የሚያፈላልጉ ይሆናል። ❤ 74 🙏 14 👍 7 😁 7 👌 4 😢 1 6 22.2K
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram