avatar
telebirr
@telebirr
19.03.2026 15:30
የኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ የ2026 የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴት የቢዝነስ መሪዎች እውቅና አገኙ!

ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ፍሬሕይወት ታምሩ መቀመጫውን በእንግሊዝ ለንደን ከተማ ባደረገው አፍሪካ ቢዝነስ መጽሔት የ2026 የአፍሪካ ሴት የቢዝነስ መሪዎች (African Business Women in Leadership 2026) መካከል በመሆን እውቅና በማግኘታቸው የተሰማንን ልዩ ኩራት ለመግለጽ እንወዳለን።

ይህ ዕውቅና በተለይም ባለፉት ዓመታት በሀገራችን በቴሌኮም እና በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ላስመዘገቡት የላቀ ስኬት እና ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ትልቅ ተምሳሌት ሆኖ የተሰጠ ዓለም አቀፍ እውቅና ጭምር ነው።

በዋና ሥራ አስፈጻሚያችን በሳል የለውጥ አመራር ብቃት፣ ኩባንያችን ከመደበኛ የቴሌኮም አገልግሎት ባሻገር ወደ ሁለገብ የዲጂታል ተጠቃሚነት እና የኢኮኖሚ እድገት ጉልህ ሚና የሚጫወት ዋና ሞተርነት መሸጋገር ችሏል።

በተጨማሪም የኩባንያችን "ቀጣዩ አድማስ፡ ዲጂታልና ከዚያም ባሻገር 2028” ስትራቴጂን በመቅረጽ እና ተግባር ላይ በማዋል፣ ተቋምን በተሳካ ሁኔታ መምራት ብቻ ሳይሆን ለሀገራችን የዲጂታል መጻኢ ዕድል ፅኑ መሠረት በማስቀመጥ ላይ ይገኛሉ፡፡

በዚህም መላው የኩባንያችን ቤተሰብ፣ ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን በአመራር ጥበባቸውና አርቆ አሳቢነታቸው ላገኙት ታላቅ እውቅና የተሰማንን ልዩ ደስታ እየገለጽን፣ በቀጣይም የላቀ ስኬት እንዲያስመዘግቡ መልካም ምኞታችንን ለመግለጽ እንወዳለን።

ለበለጠ መረጃ: https://bit.ly/4sXkmuP
45
👍 19
😁 13
👏 12
👌 6
🙏 1
5 27.7K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram
Открыть в Telegram