avatar
telebirr
@telebirr
12.03.2026 16:56
የኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለስትራቴጂያዊ ኢንቨስትመንትና የፋይናንስ ትብብር በሮም ከሲዲፒ አመራሮች ጋር ውጤታማ ውይይት አደረጉ

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ከኩባንያው ከፍተኛ የሥራ አመራር ልዑካን ቡድን ጋር በመሆን በጣሊያን ሮም ከሲዲፒ (Cassa Depositi e Prestiti - CDP) ከፍተኛ አመራሮች ጋር በስትራቴጂያዊ የትብብር መስኮችና ለታላላቅ የኢንቨስትመንት ፕሮግራሞቻችን የፋይናንስ አጋርነት ላይ ያተኮረ ፍሬያማ ውይይት አካሂደዋል።

ከፍተኛ ጉብኝት የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠንና የዲጂታል መሠረተ ልማት ሥነ-ምህዳር ለማስፋፋት ያለመውን የኩባንያችንን የ"ቀጣዩ አድማስ፡ ዲጂታልና ከዚያም ባሻገር 2028" ስትራቴጂን ለመተግበር የሚረዱ የፋይናንስ አማራጮችን ለማፈላለግ ያለመ ነው።

ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ መጠነ-ሰፊ የኔትወርክ ማስፋፊያና የማዘመን ሥራዎችን፣ የዲጂታልና የክላውድ መሠረተ ልማትን ማጠናከርን እንዲሁም እንደ ቴሌብር ያሉ የፈጠራ ውጤት የሆኑ ዲጂታል ፕላትፎርሞችንና የፋይናንስ አገልግሎቶችን የማሳደግ ውጥኖቻችንን በዝርዝር አብራርተዋል።

የሲዲፒ አመራሮች በበኩላቸው ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ዓመታት ከመደበኛ ኦፕሬተርነት ወደ ዘመናዊ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ኩባንያ ያደረገውን አስደናቂ ሽግግርና ፈጣን ዕድገት በማድነቅ፤ ኩባንያችን በዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኢንዱስትሪ ውስጥ አርአያ የሚሆን ተሞክሮ መሆኑን ገልጸዋል።

በተቋማቱ መካከል በሚኖረው አጋርነት ሊከናወኑ የሚችሉ የትብብር መስኮችም ተለይተው የቀረቡ ሲሆን፤ እነዚህም የኔትወርክ ማስፋፊያ፣ የላቁ የዳታ ሴንተር ግንባታ፣ የታዳሽ ኃይል አማራጮች እንዲሁም በቴሌብር በኩል የሚከናወኑ የዲጂታል ግብርና ድጋፎችንና የአርሶ አደሮች የብድር አቅርቦት ሞዴሎችን ያካትታል።
62
👍 19
👏 3
👌 3
2 21.1K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram
Открыть в Telegram