telebirr @telebirr 10.03.2026 23:56 Скопировать Пожаловаться ኩባንያችን ኢትዮ ቴሌኮም በባርሴሎናው MWC 2026 የዓለም አቀፍ ተቋማትን ከፍተኛ አድናቆት አተረፈ! ኩባንያችን በባርሴሎና በተካሄደው የ2026 የሞባይል ዓለም አቀፍ ኮንግረስ ላይ በታሪካችን ለመጀመሪያ ጊዜ የራሱን የቴክኖሎጂ ማሳያ ይዞ በመቅረብ በዓለም አቀፍ ደረጃ በፈጣን ሽግግር ላይ ከሚገኙ ኦፕሬተሮች አንዱ መሆኑን ለዓለም አስመስክሯል። የዘርፉ መሪዎች፣ ዓለም አቀፍ ኦፕሬተሮች እና የልማት አጋሮች ኩባንያችን ከመደበኛ ቴሌኮም ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ኩባንያ እያደረገ ያለውን ሽግግር በዓለም አቀፍ ደረጃ በፈጣንነቱና በውጤታማነቱ የሚጠቀስ ተሞክሮ መሆኑን በመግለጽ ከፍተኛ አድናቆታቸውን ሰጥተዋል። በርካታ ዓለም አቀፍ ኦፕሬተሮች የሀገራችንን የዲጂታል ፋይናንስ እየመራ ካለው ከቴሌብር ተሞክሮ ለመውሰድ ያላቸውን ከፍተኛ ፍላጎት የገለጹ ሲሆን፤ በላቁ የቴሌኮም መሠረተ ልማቶች፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና በክላውድ አገልግሎቶች ዙሪያም ከቴክኖሎጂ አጋሮች ጋር በአዲስ አበባ ዝርዝር ውይይቶችን ለመቀጠል እና የብቃት ማረጋገጫ ሙከራ (PoC) ፕሮጀክቶችን ለመጀመር ስምምነት ላይ ደርሰናል። ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ፍሬሕይወት ታምሩ እንደገለጹት፤ ኩባንያችን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞን በመምራት ረገድ ያለውን ተግባራዊ ልምድ ለዓለም አቀፍ ተዋንያን ለማካፈል እና በትብብር ለመሥራት ምንጊዜም ዝግጁ ነው። ይህ የባርሴሎና ተሳትፏችን ስትራቴጂያዊ አጋርነታችንን በማጠናከር፣ የኔትወርክ ሽግግራችንን በማፋጠን እና የኢትዮጵያን የዲጂታል ሥነ-ምህዳር ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር ረገድ ትልቅ ስኬት የታየበት የታሪክ ምዕራፍ ሆኖ ተመዝግቧል። ❤ 49 👌 8 👍 6 👏 6 😢 4 😍 1 4 20.6K
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram