telebirr @telebirr 09.03.2026 20:42 Скопировать Пожаловаться ኢትዮ ቴሌኮም ግዙፍ የኔትወርክ ማስፋፊያዎችን ለማከናወን እና ለማዘመን የሚያስችል ስምምነት ከዜድ.ቲ.ኢ ጋር ተፈራረመ! የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ከኩባንያው ከፍተኛ የማኔጅመንት አመራሮች ጋር በመሆን በባርሴሎና በተካሄደው የ2026 የሞባይል ዓለም አቀፍ ኮንግረስ ጎን ለጎን፣ ከዜድ.ቲ.ኢ (ZTE) ኮርፖሬሽን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በዜድ.ቲ.ኢ የሥራ ቀጠና ውስጥ ግዙፍ የኔትወርክ ማስፋፊያ እና የማዘመን ስራዎችን ለማከናወን የሚያስችል ስምምነትን በስኬት አጠናቀዋል። ኢኒሸቲቩ 115 የገጠር ጣቢያዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 647 የኔትወርክ ጣቢያዎችን የሚያካትት ሲሆን፣ የኔትወርክ ተደራሽነት ለማሳደግ እና የኢትጵያን የዲጂታል አካታችነት ይበልጥ ለማስፋፋት የላቀ ሚና ይኖረዋል። ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ፣ የ4ጂ የሕዝብ ሽፋንን ወደ 95.5 በመቶ በማሳደግ የኔትወርክ አቅምን፣ ተደራሽነት እና የአገልግሎት ጥራትን በከፍተኛ ደረጃ ለመጨመር በተለይም ዘመናዊ የሞባይል ብሮድባንድ ኢንተርኔትን ወደ ገጠርና አገልግሎቱ ወዳልተዳረሰባቸው አካባቢዎች በማዳረስ የሃገራችን የዲጂታል አካታችነት ለማፋጠን ቁልፍ ሚና ይጫወታል። ስምምነቱ በዋናነት የኢትዮጵያን ሰፊ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አጀንዳን ለመደገፍ እና የዲጂታል ስነ-ምህዳሩን በዘመናዊ፣ አስተማማኝ እና ለወደፊት ዝግጁ በሆኑ የቴሌኮሙኒኬሽን መሠረተ ልማቶች በማስፋፋት በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ዜጎች፣ ተቋማት እና ቢዝነሶች አቅምን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡ በቀጣይም ኩባንያችን በላቁ ቴክኖሎጂዎች እና ስትራቴጂያዊ አጋርነቶች ላይ መዋለ ንዋይ በማፍሰስ ሀገራችን በአፍሪካ ግንባር ቀደም የዲጂታል ማዕከል ለመሆን እያደረገች የሚገኘውን ሁሉገብ ጥረት እና ጉዞ ለማፋጠን ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። ❤ 62 👍 32 👏 6 🙏 6 👌 5 💯 1 4 19K
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram