avatar
telebirr
@telebirr
09.03.2026 17:00
የመላ አፍሪካውያን ኩራት የሆነው የአድዋ ድል 130ኛ ዓመት እና የኩባንያችን ምስረታ 132ኛ ዓመት በዓልን በድምቀት አክብረናል!

እንኳን አደረሳችሁ! እንኳን አደረሰን!

የመጀመሪያውን ስልክ ዓለም በተዋወቀ በ16ኛው ዓመቱ ከአፍሪካ ቀድመን የስልክ እጀታን ጨብጠን "ሃሎ ሃሎ" ተባባልን፤

ከአዲስ አበባ እስከ ሐረር የተዘረጋውን የባቡር ሃዲድ ተከትሎ የረጅም ርቀት የቴሌፎንና የቴሌግራም መስመሮች ዝርጋታ ሲከናወን፣ አገልግሎቱን ለማስተዳደር የተቋቋመው የአፍሪካ ቀዳሚ የቴሌፎን መስሪያ ቤት ዛሬ 132ኛ ዓመቱን እያከበረ ለሚገኘው ኢትዮ ቴሌኮም መሰረቱን ጥሏል።

እንደ ቴሌግራፍ፣ መደበኛ ስልክና ፋክስ በመሳሰሉ ቀደምት አገልግሎቶች ጀምሮ ከዘመኑ ጋር እየተራመደ ሀገሬውን እርስ በእርስ ከማገናኘት አልፎ ዓለም አቀፍ መስመሮችን ከገመድ እስከ ሞገድ፣ ከዚህም አልፎ እስከ ሳተላይት የዘመኑን ቴክኖሎጂ እያቀረበ ዛሬ ላይ ደርሷል።

ኢትዮ ቴሌኮም በሀገራችን ታላቅ ታሪክ ውስጥ ያለውን የዘመናት ታማኝነት በማጽናት፣ አሁን ደግሞ የኢትዮጵያን ዲጂታል መፃዒ ዕድል የሚቀይርና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱን የሚያረጋግጥ 'ቀጣዩ አድማስ፡ ዲጂታልና ከዚያም ባሻገር 2028' ስትራቴጂን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ሲሆን። ማንም ወደኋላ እንዳይቀር አስተማማኝ የመሰረተ ልማት መደላደል በመፍጠርና በዲጂታል መፍትሄዎች ላይ በማተኮር፣ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ሁለንተናዊ ዕድገት ግንባር ቀደም ለማድረግ በቁርጠኝነት እየገሰገሰ ይገኛል።
 
በ2030 ዲጂታል ኢትዮጵያ ጥረታችን ዜጎች በመረጃ ይተሳሰራሉ፤ ወሰን የለሽ ትምህርትና የጤና አገልግሎትም ያገኛሉ፤ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ህይወታቸውን ያቀላሉ፡፡
 
ኢትዮ ቴሌኮም በዚህ ብዙሃን አቀፍ በሆነ ስልታዊ ንቅናቄ ላይ የበኩሉን ደማቅ አሻራ ያኖራል!

#Adwa
#Ethiotelecom
33
👍 10
👏 3
😍 1
1 17.7K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram
Открыть в Telegram