የኢትዮጵያ አየር መንገድ እ.ኤ.አ በ2040 ዓመታዊ ገቢውን 30 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ማቀዱን አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን አስመልክቶ የአየር መንገዱ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው መግለጫ የሰጡ ሲሆን ተቋሙ ባለፋት ስምንት አስርት ዓመታት የኢትዮጵያ የዕድገት፣ የትርፋማነት እና የሀገር ኩራት ምሳሌ ሆኖ መዝለቁን ገልጸዋል።
ተቋሙ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ተወዳዳሪነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ራዕይ 2040 የተሰኘ ስትራቴጂክ እቅድ ማዘጋጀቱን አስታውቀዋል።
ዓመታዊ መንገደኞችን የማጓጓዝ አቅሙን አሁን ካለበት 20 ሚሊዮን ወደ 60 ሚሊዮን ከፍ የማድረግ የሚጓጓዝ አቅሙን ደግሞ ከ850 ሺህ ቶን ወደ 2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ቶን ለማሳደግ ታቅዷል ብለዋል።
ዝርዝሩን ለመከታተል ሊንኩን ይጫኑ��
https://youtu.be/z02xksgEhfE
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram