Abay Bank @abaybanksharecompany 07.04.2026 19:18 Скопировать Пожаловаться የዓባይ ባንክ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ ------------------------- የዓባይ ባንክ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በዛሬው ዕለት የሥራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ በጉብኝቱ የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የኋላ ገሠሠ ኢንስቲትዩቱ በአጭር ጊዜ ሰፊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ከጉብኝቱ መረዳት መቻላቸውን ተናግረዋል። የባንኩ ዘርፍ ከቴክኖሎጂ ጋር ሰፊ ቁርኝት ያለው በመሆኑ በቀጣይ ስትራቴጂያዊ አጋርነት ፈጥሮ ለመሥራት የሚያስችል መልካም አጋጣሚ መኖሩንም ገልፀዋል፡፡ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር/ኢ/ር) የተቋሙን የሥራ እንቅስቃሴ በተመለከተ ለኃላፊዎቹ ያብራሩ ሲሆን፣ ኢንስቲትዩቱ ከዓባይ ባንክ ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ዓባይ - የታላቅነት ምንጭ! ❤ 22 👍 21 6 4.7K
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram