Abay Bank @abaybanksharecompany 24.02.2026 20:41 Скопировать Пожаловаться ውድ ደንበኞቻችን፣ በኢትዮጵያ አደጋ ስጋትና ምላሽ ፈንድ አዋጅ ቁጥር 1386/2025 እና በደንብ ቁጥር 576/2025 መሰረት፣ ከየካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሁሉም ባንኮች እና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ከደንበኞች ላይ ክፍያዎችን በመሰብሰብ በብሔራዊ ባንከ በተያዘው የኢትዮጵያ አደጋ ስጋትና ምላሽ ፈንድ ጽ/ቤት ሒሳብ ገቢ እንዲያደርጉ ተደንግጓል፡፡ በመሆኑም ባንካችን ከሚሰጠው ማንኛውም ዓይነት መደበኛ ብድር ላይ የሚለቀቀውን መጠን 1 በመቶ፣ እንዲሁም በሁሉም የባንካችን የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቶች ደንበኞች ከሚከፍሉት የአገልግሎት ክፍያ ላይ 5 በመቶ እየተጨመረ የሚሰበስብ እና ለኢትዮጵያ አደጋ ስጋትና ምላሽ ፈንድ ጽ/ቤት ገቢ የሚያደርግ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የባንካችን ቅርንጫፍ በመሄድ ወይም ወደ 8834 የደንበኞች አገልግሎት የጥሪ ማዕከል መደወል የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን። ዓባይ - የታላቅነት ምንጭ! ❤ 12 👍 1 17 7.3K
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram