“ልጆች የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች”
-------------------------
ባንካችን
በእንቡጥ የልጆች የቁጠባ ሒሳብ ወላጆች ለልጆቻቸው የቁጠባ ባህልን እንዲያስተምሩ እንዲሁም ለነገ መሰረት እንዲያኖሩላቸው ያግዛል!
ልጆችን ስለቁጠባ በልጅነት ዕድሜያቸው ማስተማር በቀጣይ የወጣትነት፣ የጎልማሳ እንዲሁም የእርጅና የዕድሜ ዘመናት በሚያጋጥሟቸው የሕይወት ምዕራፎች ላይ ጤናማ የገንዘብ ግንዛቤ፣ አያያዝ፣ አጠቃቀም እንዲሁም የተሳካ ሕይወት እንዲኖራቸው ያስችላል፡፡
ልጆችዎን ስለቁጠባ ለማስተማር የሚረዱ ነጥቦችን እነሆ፡-
1. ልጆችዎ በትንሹም ቢሆን የመቆጠብ ፍላጎት ሲያሳዩና ሲጀምሩ ያበረታቷቸው፣
2. በቁጠባው ማድረግ የሚፈልጉትን አርቀው እንዲያልሙ ግብ ያስቀምጡላቸው፡፡ የቁጠባ ግባቸውን ዕውን እንዲያደርጉ ያግዟቸው፣
3. የሚቆጥቡበት ምቹ ሁኔታ ይፍጠሩላቸው፡፡ የቁጠባ ሳጥን መግዛት እና በአግባቡ ማስቀመጥ ሊሆን ይችላል፣
4. በተለያዩ ጉዳዮች ልጆች የሚያወጡትን ገንዘብ በመመዝገብ መደመርና በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ድምሩን በማሳየት የወጪውን ከፍታ ያሳዩዋቸው፣
5. ልጆችዎ ሊቆጥቡ ካስቀመጡት ግብ በላይ መቆጠብ ከቻሉ የጉርሻ ክፍያ በመክፈል ለበለጠ ቁጠባ ያነሳሱዋቸው፣
(ተጨማሪ:
https://www.facebook*.com/share/p/1H7k5xKbJw/)
ዓባይ - የታላቅነት ምንጭ
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram