Safaricom Ethiopia PLC @Safaricom_Ethiopia_PLC 11.03.2026 16:38 Скопировать Пожаловаться ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ጋር በዘመናዊ የቴሌኮሙኒኬሽን እና የህዋ ሳይንስን በመጠቀም በመላ አገሪቱ የሚገኙ ተማሪዎችን እና የዘርፉን ባለሙያዎች ለማብቃት በሚሰሩ ስራዎች ላይ ተወያይተናል። በውይይቱ ወቅት የውጭ ግንኙነት ዋና ኃላፊያችን ዶ/ር አንዱአለም አድማሴ በቴክኖሎጂና ሳይንሳዊ ተቋማት መካከል ጠንካራ ትብብር መፈጠሩ ስላለው ጠቀሜታ አጽንኦት ሰጥተዋል። ዶ/ር አንዱአለም የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ ለመደገፍ በትኩረት እየሰራን መሆኑን ጠቁመው ቀጣዩን ትውልድ በሳይንስና ቴክኖሎጂ የሚያልቁ ጅምር ስራዎችን እያስተዋወቅን እንገኛለን ብለዋል። የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ልዑካን በበኩላቸው ህብረተሰቡ ለሀገራዊ የጠፈር መሠረተ ልማት ዝርጋታ እንዲሁም የህዋ ሳይንስ በማህበረሰቡ ውስጥ እንዲስፋፋ ያበረከተውን ጉልህ አስተዋፅኦ አንስተዋል። ውይይቱ የኢትዮጵያን ቴክኖሎጂና እና ሳይንሳዊ አቅምን ለማሳደግ አስፈላጊ በሆኑ የትብብር ስራዎች ላይ መሰረት የጣለ ነው። ❤ 6 👍 4 😢 1 6 2 6.1K
Обсуждение 6
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram