ETV የልጆች ዓለም @ETVkidschannel 08.09.2025 02:59 Скопировать Пожаловаться የእመርታ ቀን *********** ጳጉሜን ሦስት ቀን "እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!" በሚል መሪ ቃል "የእመርታ ቀን" ተብሎ ይውላል፡፡ በዚህ ዕለት ኢትዮጵያ እያመጣቻቸው ያሉት እመርታዎች ይወሳሉ፡፡ ኢትዮጵያ በረሃብ ከምትታወቅበት አውድ ወጥታ፤ ስንዴን በማምረት ከውጭ ማስገባትን አቁማ ወደ ውጭ እስከ መላክ የደረሰ እመርታን አሳይታለች፡፡ በስንዴ ብቻ ሳይሆን በሩዝ፣ በበቆሎ፣ በዶሮ እና ዓሣ፣ በወተት፣ በቡና፣ ቅመማ ቅመም እንዲሁም በአትክልት እና ፍራፍሬ ምርት የታየው እምርታ የሚጨበጥ እና የኢትዮጵያን መጻኢ ተስፋ የሚያሳይ ነው፡፡ እየተገበረችው ባለው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ከስብራቷ አገግማ ወደ ማንሰራራት እየተንደረደረች ትገኛለች፡፡ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን በጥራት እና በፍጥነት በመፈጸም የላቀ እመርታን አሳይታለች፡፡ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ከሞት አንስታ የብርሃን ማማ አንዲሆን አብቅታለች፤ አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስ በማድረግ እውነተኛ የአፍሪካ መዲና የሚያደርጋትን ለውጥ እንድታስመዘግብ ማድረግ ችላለች፡፡ አረንጓዴ አሻራ ኢትዮጵያ በደን ሽፋን፣ አፈሯን በመጠበቅ እና የምግብ ዋስትናዋን በማሻሻል ረገድ አስደናቂ ለውጥ ያመጣችበት ግዙፍ ፕሮጀክቷ ነው፡፡ በኢንዱስትሪው ዘርፍ እየመጣ ያለው ለውጥ ከማምረት በላይ ነው፡፡ ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን ከመተካትአልፋ የወጪ ምርቷን አሳድጋለች፡፡ #ebcdostream #ኢትዮጵያ #EBC #እመርታ #ጳጉሜን ❤ 3 👍 1 2 3.6K
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram