avatar
Bank of Abyssinia
@BoAEth
25.03.2026 16:54
ባንካችን አቢሲንያ እና ቪዛ የ2026 ፊፋ ዓለም ዋንጫን ለመታደም ዕጣ የወጣላቸዉን የ2ኛ ዙር 4 ዕድለኞች ይፋ አደረጉ

ባንካችን አቢሲንያ እና ቪዛ ደንበኞችን ለማበረታታት ብሎም ለመሸለም የ2026 ፊፋ ዓለም ዋንጫን በስፍራው በአካል ተገኝተው ለመከታተል የሚያስችል ዕጣ የወጣላቸዉን የሁለተኛ ዙር 4 ዕድለኞች በጋራ ይፋ አደረጉ።

መጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው መ/ቤት የባንካችን የሥራ ሐላፊዎችና የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ታዛቢዎች በተገኙበት መርሐ ግብር ላይ የባንካችን ዴፒዩቲ ቺፍ ከስተመር ሪሌሽንሺፕና አኪዩዜሽን ኦፊሰር አቶ ወሰንየለህ አበራ የዕጣ ማውጣቱን ሥነ-ሥርዓት በይፋ አስጀምረዋል።

ግልጽነትን በተከተለ መንገድ በተካሄደው በዚህ የዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት መሠረትም የባንካችን የምስራቅ አዲስ ዲስትሪክት ሶስት ደንበኞች (የዕጣ ቁጥር 500003708፣900018878 እና 100022256)
ዕድለኛ የሆኑ ሲሆኑ፣ አራተኛው ዕድለኛ ደግሞ የማዕከላዊ አዲስ ደንበኛ (የዕጣ ቁጥር 400010191)ሆነዋል።

ከዕጣ አወጣጡ ሥነ-ሥርዓት በኋላ ዕድለኞቹን "እንኳን ደስ አላችሁ!" በማለት ንግግራቸውን የጀመሩት አቶ ወሰንየለህ "ከቪዛ ጋር ባለን ትብብር የዲጂታል ክፍያ ስርዓትን ቀልጣፋ ለማድረግ በምናደርገው ጥረት ውስጥ ለደንበኞቻችን የ2026 ዓለም ዋንጫን በስፍራው ተገኝተው እንዲከታተሉ ዕድል በመስጠታችን ደስታ ይሰማናል!" ብለዋል።

በቪዛ የምስራቅ አፍሪካ ክላስተር ኃላፊ አቶ ያሬድ እንዳለ በበኩላቸው "ከአቢሲንያ ባንክ ጋር እያካሄድን ያለነው የሽያጭ ዘመቻ ደንበኞች በዲጂታል መንገድ ለመክፈል መምረጣቸው ከምቾቱ እና ደህንነቱ ባሻገር፣ እንደ ፊፋ ዓለም ዋንጫ 2026 ባሉ አለም አቀፍ መድረኮች ላይ መታደም ያሉ ሌሎች ተጨማሪ ዕድሎችን እንደሚፈጠር ማሳያም ጭምር ነው" ብለዋል።

በዚህ የሽያጭ ዘመቻ ጠንካራ የደንበኞች ተሳትፎ የታየ ሲሆን፣ ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ ከ6,000 በላይ ኩፖኖች የአቢሲንያ ባንክ ቪዛ ካርዶችን በመጠቀም ከ1,000 ብር በላይ ግብይቶችን ለፈጸሙ ደንበኞች ተሰራጭተዋል።

ይህ የሽያጭ ዘመቻ የዲጂታል ክፍያዎችን ተደራሽ ማድረግ እና የፋይናንስ አካታችነትን መደገፍ ላይ ያተኮረ ሲሆን በባንካችን እና በቪዛ መካከል በመላው ኢትዮጵያ የክፍያ ስርዓቶችን ፍጥነት፣ ደህንነት እና ቅልጥፍና ለማሻሻል ያለመ ሰፊ ስትራቴጂካዊ ትብብር አካልም ነው።

ተጨማሪ ዕጣዎች በቀሪዎቹ ሳምንታት በሚኖሩ ቀጣይ ዙሮችም የሚወጡ ሲሆን፣ ይህም ለደንበኞች በየዕለቱ የቪዛ ካርድ ሲጠቀሙ የዓለም ዋንጫ ታዳሚ የመሆን ዕድል የሚሰጥ ይሆናል።
43
👍 9
👏 3
🔥 2
😁 2
4 22.6K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Bank of Abyssinia

186.2K
Bank of Abyssinia – The Choice for All
Welcome to BoA’s official Telegram channel!

Use @BOA_ATM_bot to access:

ATM locators
Card services & support
Real-time updates
Открыть в Telegram