avatar
Bank of Abyssinia
@BoAEth
23.03.2026 13:43
የባንካችን ሐዋሳ ዲስትሪክት በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 1.3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

የባንካችን ሐዋሳ ዲስትሪክት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የብር 1.3 ሚሊዮን የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አደረጉ።

መጋቢት 9 ቀን 2018 ዓ.ም በዞኑ ዋና ከተማ አርባ ምንጭ በተከናወነው የድጋፍ ርክክብ ሥነ-ሥርዓት ላይ የባንካችን ሐዋሳ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ሳኒ ቦቸሬን ጨምሮ ሌሎች የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች፣ የጋሞ ዞን የመንግሥት ኮሚኒኬሽንና የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጸሐፊ አቶ ገዛኻኝ ጋሞና ሌሎች የስራ ሐላፊዎች ተገኝተዋል።

‎የባንካችን ሐዋሳ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ሳኒ ቦቸሬ "በዞኑ በደረሰው የተፈጥሮ አደጋ የባንኩ ኃላፊዎችና ባልደረቦች ልባዊ ኅዘን የተሰማቸው መሆኑን ገልጸው ከሐዋሳ ዲስትሪክት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የብር 1 ሚሊዮን የጥሬ ገንዘብ እንዲሁም የብር 300 ሺህ የአይነት ድጋፍ አበርክተናል" ብለዋል።

የጋሞ ዞን የመንግሥት ዋና ተጠሪ እና የብልጽግና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገዛኻኝ ጋሞ በበኩላቸው አቢሲንያ ባንክ ከሕዝብና መንግሥት ጎን በመቆሙ አመስግነዋል።
43
👍 14
👏 3
2 13.8K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Bank of Abyssinia

186.2K
Bank of Abyssinia – The Choice for All
Welcome to BoA’s official Telegram channel!

Use @BOA_ATM_bot to access:

ATM locators
Card services & support
Real-time updates
Открыть в Telegram