avatar
Bank of Abyssinia
@BoAEth
21.03.2026 10:35
ለአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ባፀደቀው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ የደንበኛ ሳቢ መግለጫ እና በተሠጠው ፈቃድ መሠረት  3,125,000 (ሶስት ሚሊዮን አንድ መቶ ሃያ አምስት ሺህ) መደበኛ አክሲዮኖችን በአንድ የአክሲዮን ዋጋ  ብር  አንድ ሺህ ስድስት መቶ (1,600)  ሽያጭ  ያከናውናል፡፡ ሆኖም ለአክሲዮን ሽያጭ የተፈቀደውን ጊዜ ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ ቀደም ሲል እስከ መጋቢት 9 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የነበረው የአክሲዮን መግዣ የጊዜ ገደብ እስከ ሚያዝያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን እያስታወቅን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን  እውቅና ከተሠጣቸው የሰነደ ሙዓለ ንዋይ አገበያዮች (ደላሎች) በኩል የግብይት ሂሳብ (Trading Account) በመክፈት የአክሲዮን ግዢውን ማከናወን የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡

ማሳሰቢያ 
ሁሉም ባለአክሲዮኖች የአቢሲንያ ባንክ ደንበኛ ሳቢ መግለጫውን በሙሉ እንዲያነቡ ይበረታታሉ ፤ለውሳኔ የተቸገሩ ከሆነ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ፈቃድ ከተሰጣቸው ገለልተኛ የፋይናንስ አማካሪዎች ምክር ይጠይቁ፤ የደንበኛ ሳቢ መግለጫው መጽደቅ ሰነድ ሙዓለ ንዋዬችን ባለሀብቶች እንዲገዙ የተሠጠ ምክር ወይም ድጋፍ ተደርጎ አይወሰድም፡፡ ይህ ማስታወቂያ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ፈቃድ አግኝቷል፡፡

ለበለጠ መረጃ ለገሐር በሚገኛው የአቢሲንያ ባንክ አክስዮን ማህበር ዋና መስሪያ ቤት በአካል ቀርቦ ማናገር ወይም በስልክ ቁጥር +25111526314 መደወል ይቻላል፡፡
23
👍 3
👏 2
10 16.8K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Bank of Abyssinia

186.2K
Bank of Abyssinia – The Choice for All
Welcome to BoA’s official Telegram channel!

Use @BOA_ATM_bot to access:

ATM locators
Card services & support
Real-time updates
Открыть в Telegram