avatar
Bank of Abyssinia
@BoAEth
20.03.2026 00:27
ከአጭበርባሪዎች ይጠንቀቁ!
/
ወቅቱ የበአል ሰሞን ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ደንበኞች ብዙ ግብይት እንደሚፈጽሙ ይታወቃል ስለሆነም አጋጣሚውን በመጠቀም ደንበኞችን የሚያጭበረብሩ አካላት ይበራከታሉ፡፡

አጭበርባሪዎቹ ከባንክ በማስመሰል ወደ ደንበኞች ስልክ በመደወል፣ በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ሀሰተኛ መልእክትን በማስተላለፍ እንዲሁም ግብይት በሚፈጸምበት ወቅት የደንበኞችን እንቅስቃሴ በማጥናት የተለያዩ የማጭበርበሪያ መንገዶችን በመጠቀም ከደንበኞች አካወንት ገንዘብ ለመውሰድ ይሞክራሉ

ስለሆነም የሚከተሉትን የጥንቃቄ መንገዶች በመተግበር ራሰዎን ከአጭበርባሪዎች ይጠብቁ

-ክፍያ በሚፈጽሙበት ጊዜ የሂሳቡን ባለቤት መረጃ ትክክለኛነት ያረጋግጡ
-ገንዘብ በሚያስተላልፉበት ወቅት ያለምንም ችኮላ ተረጋግተው ግብይቶን ይፈጽሙ
-የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ልናስተካክልዎት ስለሆነ የምንነግርዎትን ቁጥር ወይም ኮድ ያስገቡ ተብለው ከሚመጡ ማጭበርበሪያዎች ምንም ኮድ ባለማስገባት ራሰዎን ይጠብቁ
-መረጃችሁን በትክክል ስላልሞላችሁ እናስተካክልላችሁ፣የሞባይል ባንኪንግ ሲስተም አፕዴት (Update) ልናደርግሎት ነው ከሚሉ የማጭበርበሪያ መልዕክቶች ይጠበቁ
-የበዓል ሽልማት ስለደረሰዎት ሽልማቱ እንዲላክልዎት ገንዘብ ያስገቡ ተብለው ከሚመጡ መልዕክቶች ይጠንቀቁ
-የባንኩን የተረጋገጡ(Verified) የመረጃ ምንጮች ብቻ ይጠቀሙ፡፡

በመሆኑም ደንበኞቻችን በማንኛውም ዘዴ የሚያገኙትን መልእክት ወደ ባንክ በመሄድ ወይም ወደ 8397 በመደውል ሳያጣሩ ምንም አይነት እርምጃ ከመውሰድ እንዲቆጠቡ ለማሳሰብ እንወዳለን።
53
👍 21
👏 10
🤩 1
2 20.2K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Bank of Abyssinia

186.2K
Bank of Abyssinia – The Choice for All
Welcome to BoA’s official Telegram channel!

Use @BOA_ATM_bot to access:

ATM locators
Card services & support
Real-time updates
Открыть в Telegram