Bank of Abyssinia @BoAEth 19.03.2026 16:33 Скопировать Пожаловаться በወርሐ ረመዳን "አሚን ለበጎነት" በሚል መሪ ሓሳብ እየተከናወነ የቆየው የረመዳን አስቤዛ የመለገስ መርሐ ግብራችን የማጠናቀቂያ ምዕራፍ በሐረር እና ጅግጅጋ ከተሞች በመጨረሻዎቹ የረመዳን ቀናት ተከናውኗል። በዚህም በጅግጅጋ ከተማ በሆስፒታል አልጋዎች ላይ ሆነው ህክምናቸውን ለሚከታተሉ ታካሚዎችና ለአስታማሚዎች የኢፍጣር ማዕድ የማጋራት መርሐ ግብር ያከናወንን ሲሆን፤ በሐረር ከተማ ደግሞ በማረሚያ ቤት ለሚገኙ ታራሚዎች ባደረግነው የኢፍጣር ማጋራት ሥነ ስርዓት ፍጻሜውን አግኝቷል። ከምንግዜውም በላቀ የኸይር ተግባራት በጉልህ በሚስተዋሉበት ታላቁ የረመዳን ወር፤ ባንካችን እየከወነው የቆየው ከወገኖቻችን ጋር በአብሮነት የመቆምና የኢፍጣር አስቤዛ የማቅረብ ተግባር፤ በመላ አገሪቱ የሚገኙ የባንካችንን ዲስትሪክቶች በሙሉ ያሳተፈ ሲሆን፤ በርካታ ወገኖቻችንን ተጠቃሚ ማድረግ የቻለ ነበር። የ "አሚን ለበጎነት" የወርሐ ረመዳን የኸይር ሥራ ተግባር መርሐ ግብራችን በታቀደው መልኩ እንዲሳካ ከባንካችን ጋር በአብሮነት ለተጉ የክልል ከተማ አስተዳደሮች፣ በየደረጃው ለሚገኙ የመጅሊስ ምክር ቤቶች፣ ለበጎ አድራጎት ተቋማትና ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት በሙሉ ባንካችን ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል። አቢሲንያ አሚን ዕሴትዎን ያከበረ! ❤ 18 👍 10 👌 1 4 16K
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram